1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤትና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 16 2009

በብዙዎቹ የአፍሪቃ መንግሥታት ዘንድ ይህ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተቀባይነት እያጣ መጥቷል

https://p.dw.com/p/2Rjos
Internationaler Strafgerichtshof Den Haag Niederlande
ምስል Imago

Beri. Berlin (Kommentar: Reformiert das Weltgericht!) - MP3-Stereo

የዓለም አቀፉን የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ሥራ-እና ዓላማ የሚቃወሙ የአፍሪቃ ሐገራት  ከፍርድ ቤቱ አባልነት እየወጡ ነዉ።እስካሁን ቡሩንዲ፤ ደቡብ አፍሪቃ እና ጋምቢያ  የመሰናበቻ ደብዳቤያቸዉን አስገብተዋል። ሌሎቹ ሃገራትም እነሱን ተከትለዉ ለመዉጣት ዳርዳር ማለታቸዉ ተሰምቷል። በብዙዎቹ የአፍሪቃ መንግሥታት ዘንድ ይህ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተቀባይነት እያጣ መጥቷል። የዶቼ ቬለዉ አቡበከር ያሎ እንደሚለዉ ፍርድ ቤቱ የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖረዉ ወደ ፊት ለዉጥ አድርጎ በአዲስ የአሰራር ዘዴ መዋቀር ይኖርበታል። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ሐተታዉን እንደሚከተለዉ አዘጋጅቶታል። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሰ