1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነት የመለውጥ ሂደት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 11 2002

ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ በወቅቱ የዓለምን የኤኮኖሚ ግንኙነት ገጽታ እየቀየረ ሲሄድ ነው የሚታየው። ራመድ ያሉ አዳጊ ሃገራት የመፍትሄው አካል እየሆኑ ሲሄዱ በዓለም የገንዘብ ተቋማት ውስጥ የሚኖራቸው ሚናም በመጠናከር ላይ ነው። ዓለምአቀፉ የኤኮኖሚ ስርዓት ከየት ወዴት? የድሆች አገሮችስ ዕጣ?

https://p.dw.com/p/KC3W
የዓለም ምንዛሪ ተቋም መቀመጫ
የዓለም ምንዛሪ ተቋም መቀመጫምስል ullstein bild - Imagebroker.net

ክፍል ፩-የዓለም ኤኮኖሚ ግንኙነት ገጽታ በተለይም ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ ባስከተለው ችግር ከሥር-መሠረቱ እየተለወጠ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ የዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋማት የ IMF ና የዓለም ባንክ ሚናም ይገኝበታል። ለመሆኑ እነዚህ ተቋማት እንዴት? ለምን ዓላማና ለማንስ ጥቅም ተቋቋሙ? በሂደት ብዙዎች ሁኔታዎችም ተከስተዋል። ለምሳሌ የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የፖለቲካ ተጽዕኖ አንዱ ነበር። ሌሎች ሁኔታዎችም አሉ። ለነዚህና ለተያያዙ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት በስኮትላንድ ዳንዲ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ንግድ ሕግ መምሕር የሆኑትን ዶር/ መላኩ ደስታን አነጋግረናል።

MM SL