1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም እግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ

ሰኞ፣ ሐምሌ 5 2002

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ለአንድ ወር ሲካሄድ የቆየው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድር በደመቀ ትርዒትና በስፓኝ የዋንጫ ባለቤትነት ተፈጽሟል።

https://p.dw.com/p/OGk4
ምስል AP

ስፓኝ የመጀመሪያ ለሆነው የዓለም ዋንጫ ድሏ የበቃችው ኔዘርላንድን በተጨማሪ ሰዓት ውስጥ 1-0 በመርታት ነው። የዝግጅቱ ስኬት የአገሪቱን የመስተንግዶ ብቃት አጠያያቂ ሲያደርጉ የቆዩትን ተጠራጣሪዎች ሁሉ ጸጥ ሲያሰኝ ሂደቱ ደቡብ አፍሪቃን ብቻ ሣይሆን መላውን የአፍሪቃ ክፍለ-ዓለም ነው ያኮራው። የ 92 ዓመቱ አንጋፋ የደቡብ አፍሪቃ የነጻነት መሪ ኔልሰን ማንዴላም ባለፈው ምሽት በጆሃንስበርጉ ሶከር-ሢቲይ ስታዲዮም በአካል መገኘታቸው መዝጊያውን ስነ-ስርዓት የበለጠ ክብር አጎናጽፎታል። የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር የእግር ኳስ ጥበብ በጉልበት የአጨዋወት ዘይቤ ላይ፤ የቡድን አጨዋወትም በግለሰብ ተውኔት ላይ አይለው የታዩት ነበር።