1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም እግር ኳስ ግጥምያ ውድድር ምድብ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 26 2002

ደቡብ አፍሪቃ ትናንት ማምሻውን ኬፕ-ታውን ላይ በተካሄደው በባሕላዊ ትርዒት የደመቀ የምድብ ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት መጪውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ለማስተናገድ በሚገባ መዘጋጀቷን አበሰረች።

https://p.dw.com/p/Kr1g

በዕጣው መሠረት ጆሃንስበርግ ላይ ሰኔ 4 ቀን. ውድድሩን የሚከፍቱት ደቡብ አፍሪቃና ሜክሢኮ ይሆናሉ። የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ አገራቸው ለአስተናጋጅነት በመብቃቷ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹ የወቅቱ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ደግሞ ከስድሥቱ ተሳታፊ የአፍሪቃ አገሮች አንዱ የዋንጫ ባለቤት እንደሚሆን ተንብየዋል። የዕጣ አወጣጡ ሥነ-ሥርዓት በሙዚቃ፣ በዳንኪራና የደቡብ አፍሪቃን ውበት በሚያሳዩ የቪዲዮ ፊልሞች ሲታጀብ ኦስካር ተሸላሚዋ የሆሊዉድ ተዋናይ ቻርሊዝ ቴሮን፣ የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል ዴቪድ ቤክሃም፣ ሃይሌ ገብረ-ሥላሴና ሁለት የደቡብ አፍሪቃ ስፖርተኞች በተለይ የምሽቱ ከዋክብት ነበሩ። ከስምንቱ ምድቦች መካከል ብራዚል የምትገኝበት ምድብ-ሰባት በጥንካሬው ከወዲሁ የሞት ምድብ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የብራዚል ተጋጣሚ ሆነው የተደለደሉት አገሮች ሰሜን ኮሪያ፣ አይቮሪ ኮስትና ፖርቱጋል ናቸው።

WM2010 Südafrika Auslosung Gruppenphase Englisch E-H
WM2010 Südafrika Auslosung Gruppenphase Englisch A-D

አዜብ ታደሰ