1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የሰብዓዊነት ቀን ታስቦ ዋለ

ሰኞ፣ ነሐሴ 15 2009

ዓለም ግጭት እና ጦርነት እየከፋባት ሞት እና ጉዳትም እየለመደች የሔደ ይመስላል። ባልፈጠሩት ጦርነት ኑሯቸው የተቃወሰ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መሸሸጊያ ጥግ ይፈልጉ ይዘዋል። ነፍሳቸውን ለማዳን ባሕር እና ድንበር የሚያቋርጡም የትዬለሌ ናቸው።

https://p.dw.com/p/2ibYD
Jemen Frauen Engagement für Kriegsopfer
ምስል DW/M. Alhadry

በዕለቱ ተፋላሚ ወገኖች ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ ማድረግ እንደሌለባቸው ጎልቷል።

ሕጻናት ከየመን እስከ ሶርያ ሕጻናት ከትምህርት ገበታቸው ይገለላሉ። ቤተሰብ እና ኅብረተሰብም ይበታተናል። ከኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ሱዳን ድርቅ እና ችግር የፈተናቸው ከመኖሪያ ቀያቸው ይፈናቀላሉ። በቀደመው የአኗር መንገድ ሕይወትን መግፋት ቢቸግራቸው የሰው እጅ ያያሉ፤እርዳታ ይጠብቃሉ። በዚህ ሁሉ መካከል የጤና እና የእርዳታ ሰራተኞች አይጠፉም።በሳምንቱ መገባደጃ ዓለም የሰብዓዊነት ቀንን አስቦ ውሏል።

ገበያው ንጉሴ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሀመድ