1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የአየር ንብረት ይዞታና አፍሪቃ፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 9 2004

የዓለምን የአየር ንብረት ይዞታ፣ አፍሪቃ ባልሰራው የአየር ብክለት ሰለባ ስለመሆኑና ስለ ካሳ ክፍያ ፤ በቀጣዩ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ፣ በሚቀርበው የመወያያ ሰነድ ውስጥ እንዲካተት ባለሙያዎች፣ አዲስ አበባ ውስጥ፤ በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ በስብሰባ

https://p.dw.com/p/15q74
ምስል picture-alliance/dpa

፣ አፍሪቃ ባልሰራው የአየር ብክለት ሰለባ ስለመሆኑና ስለ ካሳ ክፍያ ፤ በቀጣዩ ዓለም አቀፍ ጉባዔ ፣ በሚቀርበው የመወያያ ሰነድ ውስጥ እንዲካተት ባለሙያዎች፣ አዲስ አበባ ውስጥ፤ በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ በስብሰባ እየመከሩ መሆናቸውን ፤ ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። በሰሜንና ደቡብ ዋልታዎች ፤ የበረዶ ክምር እየተናደና እየቀለጠ፤ በምድር ሰቅ አካባቢ ሃገራትም ፤ የደን መጨፍጨፍ ፤ ለምድረ በዳ መስፋፋት ሰበብ በመሆኑ፤ ዓለማችንን ለአየር ንብረት መዛባት እያጋላጣት መሆኑ የታወቀ ነው። ዋናው አደጋ ግን የተደቀነው፤ ከየፋብሪካው የሚትጎለጎለው ጭስ መሆኑ የሚታበል አይደለም ። በዚህ ደግሞ በኢንዱስትሪ የገሠገሡት አገሮች እንጂ የአፍሪቃ አህጉር ተጠያቂ አይሆኑም ።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ