የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስና ሙስና
ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2001ማስታወቂያ
የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሊቀመንበር Huguett Labelle ዛሬ እንዳስታወቁት በአሁኑ ጊዜ በተለይ በቅርቡ ነፃነታቸውን በተጎናፀፉ አንዳንድ አገራት ባለሀብቶች የሚፈልጉትን ለማግኘት ለመንግስት ባለስልጣናት ጉቦ መስጠት መገደዳቸው አንዱ ትልቁ ችግር ሆኖ ተገኝቷል ። ባለሀብቶች ብቻ ሳይሆኑ ድሀው ህብረተሰብም የተለያዩ አገልግሎቶች ለማግኘት ከቀድሞው ይልቅ አሁን ጉቦ በመስጠት ለተጨማሪ ወጪ ተዳርጓል ።
ሂሩት መለሰ / አርያም ተክሌ