1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድርና ግብ ወሳኝ ቴክኖሎጂ

ረቡዕ፣ ሰኔ 4 2006

ብራዚል የምታስተናግደው ፤ የዘንድሮው የዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ነገ የሚጀመር ሲሆን፣ የ 5ቱም- ክፍላተ-ዓለም እግር ኳስ አፍቃሪዎች፤ ይህን ልብ አንጠልጥል የአስፖርት ውድድር አንድ ወር ሙሉ ለመከታተል ተዘጋጅተዋል። በዘንድሮው የዓለም

https://p.dw.com/p/1CGbd
ምስል picture-alliance/dpa

የእግር ኳስ ዋንጫ አንዱ አዲስ ነገር፤ አምና በዚህ ወር በኮንፈደሬሽን የዋንጫ ውድድር ወቅት የተሞከረው የኳስን ግብ መሆን-አለመሆን፣ የሚቆጣጠረው የአጫዋች ዳኛ አስተማማኝ ረዳት የሆነው ሥነ ቴክኒክ፣ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑ ነው።

2,44 ሜትር ከፍታና 7,32 ሜትር ሳፋት ባለው ግብ ኳስ በአየርም ሆነ መሬት የግቡን መሥመር ካለፈች፣ ዳኛው እንደ እጅ ሰዓት በሚያሥረው መሳሪያ Goal የሚል ማረጋገጫም ሆነ መረጃ ያገኛል። Goal Line Technology ወይም Goal Decision System የተሰኘው 3 አቅጣጫ ምስል የሚያሳየው ካሜራ ግብ አካባቢ የኳሷን አካሄድ---አቅጣጫና ማረፊያ በጥሞና የሚከታተል ሲሆን፤ «ኳስ መሥመር አልፋ ግብ ሆናለች --አልሆነችምእየተባለ ሲያነታርክ የኖረን አስቸጋሪ ጉዳይ የሚያስወግድ መሆኑ ይታመንበታል።

Dilma Rousseff Präsidentin Brasilien 02.06.2014
ምስል picture alliance/AP Photo

በአንድ የእግር ኳስ ሜዳ የሚተከል ይህ ዓይነቱ መሣሪያ ወደፊት ዋጋው ካልቀነሰ 240,000 ዩውሮ የሚያስወጣ መሆኑ ነበር ከዚህ ቀደም የተገለጠው። «ፊፋ» አወዳድሮና ይበልጥ አስተማማኝ ነው ብሎ የመረጠው፤ Goal Control የተባለውን አንድ የጀርመን ኩባንያ ያቀረበውን ነው። ኳስ ግብ መሆን --አለመሆኗን ትክክለኛ መረጃ ሰጪ ነው የተባለውን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም የአስፖርት ባለሙያዎች እንዴት ያዩታል? ቀደም ባለው ጊዜ በኢትዮጵያ የክለቦች ቀጥሎም የብሔራዊው ቡድን S።ልጣኝ የነበረውን በአውሮፓ የአግር ኳስ ማሕበር (UEFA) ፕሮፌሽናል የማሠልጠን ፈቃድ አግኝቶ አሁን በቼክ ሪፓብሊክ የተለያዩ ክለቦችን የሚያሠለጥነውን / ተስፋዬ ጥላሁንን አነጋግሬው ነበር።

«የዚህ ቴክኖሎጂ----------»»

በሐምሌ ወር 1958 ማለት ሐምሌ 30 ቀን 1966 በኢንግላንድና ምዕራብ ጀርመን የፍጻሜ ግጥሚያ፤ መሥመር ላይ የነጠረ ኳስ ግብ ተብሎ አድልዎ ተፈጽሞብናል በማለት ጀርመናውያን በየጊዜው ሲያነሱት የኖረው ጉዳይም አለ፦ ጊዜው ራቅ ቢልም! FIFA የግብን ውጤት ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ለውሳኔው ሌሎች የገፋፉት ምክንያቶችም ይኖራሉ---

«ጎል ኮንትሮል» ጎል ላይን ቴክኖሎጂ አስተማማኝነቱ ተሞክሮ ቢረጋገጥለትም አሁንም የሚቃወሙ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች አልታጡም---

Deutsche Nationalmannschaft Abflug nach Brasilien WM 2014
ምስል picture-alliance/dpa

በዓለም ዙሪያ እጅግ ተወዳጅ የሆነው የእግር ኳስ ጨዋታ የሚካሄድበት የሜዳው ስፋትና ርዝመት 120 እና 90 ሜትር መካከል ሲሆን የአንዳንድ ኳስ ሜዳዎች ስፋት በጥቂት ሜትሮች ወይም ሴንቲሜትሮች ከመደበኛ የእግር ኳስ ሜዳ ልዩነት አለው። የሆነው ሆኖ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን(FIFA) ደንብ መሠረት፣ የሜዳው ርዝማኔ 105 ሜትር ወርዱ ደግሞ 68 ሜትር ነው። ለውጥ እስኪደረግ ድረስ እስካሁን በዚሁ እንደጸና ነው። የተጋጣሚ ቡድኖችን ግብ ጠባቂዎች ሁለቱን ብንቀንስ 20 ተጫዎቾች ናቸው በተጠቀሰው ሜዳ ውስጥ የሚራኮቱት ይህ ምናልባት ለውጥ የሚያስፈልግበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?!

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ