1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የፕሬስ ቀን

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 28 2009

የዘንድሮ የፕሬስ ነጻነት ቀን እንደተለመደው ተከብሮ ይዋል እንጂ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት ጋዜጠኞች እና ጠንካራ ትችት አቅራቢ ጸሓፍት እንግልት፣ እስር እና መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል። የኢትዮጵያ ኹኔታ ከቀድሞው በባሰ መልኩ እንደሚገኝ ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/2cXMw
World Press Freedom Day Karikatur
ምስል Gado

በየዓመቱ የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን ዘንድሮም በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። የዘንድሮው የፕሬስ ቀን የተከበረው 80 በሚኾኑ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ነው። የተባበሩት መንግሥታቱ ድርጅት የትምህርት፤ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) የዚህን ዓመት በዓል በኢንዶኔዢያ መዲና ጃካርታ ለአራት ቀናት በዘለቀ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብሯል።  

የዘንድሮ የፕሬስ ነጻነት ቀን እንደተለመደው ተከብሮ ይዋል እንጂ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት ጋዜጠኞች እና ጠንካራ ትችት አቅራቢ ጸሓፍት እንግልት፣ እስር እና መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል። የኢትዮጵያ ኹኔታ ከቀድሞው በባሰ መልኩ እንደሚገኝ ተገልጧል።

ቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው በአሁኑ ወቅት ስዊድን ውስጥ ለሲቪክ ድርጅቶች መብት በሚከራከረው መንግሥታዊ ያልኾነ ድጅት ውስጥ የአፍሪቃ መርሐ-ግብር ኃላፊ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ የኢትዮጵያ ኹኔታ ከበፊቱ ማሽቆልቆሉን ተናግሯል። «ባለፉት ዓመታት እንደነበረው ነው የቀጠለው። የባሰ እያሽቆለቆለ ነው ያለው። ከሌሎች ሃገራት ጋራ በተነጻጻሪ ሲታይም ኢትዮጵያ የምታገኘው ደረጃ  ፤ የሚሰጣት ነጥብ አሳዛኝ ነው» ብሏል።

ጀርመንን ጨምሮ በአውሮጳ እንዲሁም በአሜሪካ የሚታተሙ ጋዜጦች አፍሪቃን በተመለከተ ለአንባቢዎቻቸው ያቀረቧቸው ጽሑፎች ደቡብ አፍሪቃ እና ደቡብ ሱዳን፤ ኮንጎ እና ኢትዮጵያ ላይ አተኩረዋል። ጋዜጦች በሚዳሰሱበት የጋዜጦች አምድ ዝግጅት ዳሰሳ ተደርጎባቸዋል። 

ገበያው ንጉሤ/ ይልማ ኃይለሚካኤል 

ማንተጋፍቶት ስለሺ