1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓ/አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 25 2007

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማዉረር ኢትዮጵያን ሰሞኑን ለሶስት ቀናት ጎብኝተዋል። ፒተር ማዉረር በቆይታቸዉም ከአፍሪቃ ሕብረት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተዉ፤

https://p.dw.com/p/1Dgid
Äthiopien Peter Maurer ICRC
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማዉረርምስል DW/G. Tedla HG

በተለይ በእስር ቤቶችና በእስረኞች ሁኔታ ላይ መወያየታቸዉን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አመልክተዋል። 150 ኛ ዓመቱን ያከበረዉ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ወሲባ ጥቃቶችን መከላከል የሲቭል ማኅበረሰብን መጠበቅ የምግብ ርዳታ ማቅረብ፤ የተለያዩ ቤተሰቦችን ማገናኘት፣ የእስረኞችና የእስር ቤቶችን ይዞታ መከታተልና በመሳሰሉት ላይ ይሠራል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ