1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዕውቀት ልውውጥና የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች፣

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 23 2006

ባለፈው ኅዳር 14 እና 15 ,2006 በለንደን ብሪታንያ፤ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ባዘጋጁት ዓለም አቀፍ የዕውቀት ልውውጥ ነክ ጉባዔ ተሳትፈው ከተመለሱት አንዱ ናቸው። በጎንደር ዩንቨርስቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፣ «ባዮ -ሜዲካል እና ላበራተሪ ት/

https://p.dw.com/p/1Ak7J
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

ቤት የ « ማይክሮባይኦሎጂ ክፍል ፕሮፌሰር ናቸው። በሽታን መቋቋም የሚቻልበት ዕውቀት (ኢሙዩኖሎጂ» ኮርሶችን ይሰጣሉ፣ የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎችን በምርምር ሥራቸው ማማከር ባች ሳይሆን፤ ከባልደረቦቻቸው ጋር በተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ ዘርፈ-ብዙ የምርምር ተግባር ያከናውናሉ።በዩንቨርስቲው በተጨማሪ የምርምርና የሕብረተሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንትም ናቸው።

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ምሁራንና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ምሁራን ዓለም አቀፍ የዕውቀት ልውውጥ ፤ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለው የትምህርት ጥራት ጠቀሜታ እስከምን ድረስ ይሆን?! የትብብሩ ምልክት አለ? ለፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሡ ግዛው ያቀረብኩላቸው የመጀመሪያ ጥያቄ ነው።

CeBIT 3013
ምስል ASBÖ/KNEF

ለአንድ ታዳጊ ሀገር እመርታ ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ዐቢይ ድርሻ እንደሚኖራቸው ከቶውንም አያጠራጥርም። የደረጁት መንግሥታት ፤ በኤኮኖሚም ሆነ በአጠቃላይ በመሠረተ ልማት ግንባር ቀደም ቦታ ለመያዝ የበቁት፣ ሳይንስንና ቴክኖሎጂን የሙጥን በማለታቸው ነው። በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች፣ ህክምና ፤ ሥነ -ቅመማ፣ ፊዚክስ፤ እንጂኔሪንግና ሒሳብ የሚሰጠው ግምት እስከምን ድረስ ይሆን? ፕሮፌሰር አፈወርቅ እንዲህ ይላሉ---

በሐምሌ ወር 1946 ዓ ም ፣ የህዝብ የጤና ጥበቃ ኮሌጅ በሚል ሥያሜ የተቋቋመው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህክምና ጉዳይ ት/ቤት ፤ አሁን በአጠቃላይ የጎንደር ዩንቨርስቲ በመባል የታወቀው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በመጪው ሐምሌ ወር 60 ዓመት የሚደፍን ቢሆንም ፣ የወርቅ ኢዮቤልዩን

ዓመቱን በሙሉ ይሆናል የሚያስበው፤ በመሆኑም ከታኅሣሥ 25 -27 ,2006 ክብረ - በዓሉን ባዘጋጀው ዐውደ ጥናት እንደሚጀምር ለመገንዘብ ችዬአለሁ ። በጎንደር ዩንቨርስቲ (Gondar school of Science and Technology)ከአውሮፓ፤ አሜሪካ፤ ከተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት ትልልቅ ሳይንቲስቶች ተሰባስበው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች ከተውጣጡ ማሁራን ጋር በተጠቀሰው ርእሰ ጉዳይ ይመክራሉ። በዐውደ ጥናቱ ላቅ ያለ ትኩረት ስለሚደረግበት ጉዳይ፣ ፕሮፌሰር አፈወርቅ እንዲህ ያብራራሉ--።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ