1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘረኝነትና አድልዎ ይዞታ በጀርመን

ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2001

ጀርመን በዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ የሚደርስ ዘረኝነትን ለመቋቋም ይበልጥ መስራት እንደሚገባት በቅርቡ ይፋ ሆኗል ።

https://p.dw.com/p/IkaV
ምስል AP

ዘረኝነትን ፣ ከዘር ጋር የተገናኘ አድልዎን እና የውጭ ዜጎች ጥላቻን የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስሪያ ቤት ልዩ አግባቢ ልዑክ ባለፈው ሰሞን ጀርመንን ከጎበኙ በኃላ እንዳስታወቁት የውጭ ዜጎች እና የውጭ የዘር ሀረግ ያላቸው ሰዎች የፖለቲካ ስርዓቱን ጨምሮ በጀርመን ዋና ዋናዎቹ ተቋማት ውስጥ እጅግ አነስተኛ በሆነ ደረጃ ነው የተወከሉት ። ከዚህ በመነሳትም ልዩ ልዑኩ ጀርመን ይህን መሰሉን ችግር ለማቃለል ብዙ መስራት እንደሚጠበቅባት አሳስበዋል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን በዚህ ላይ ያተኩራል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ