1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘንድሮው ብርቱ ዝናምና መንስዔው፣

ረቡዕ፣ ነሐሴ 15 2005

የአየር ንብረት፣ ከአህጉራዊና ከክፍለ-ዓለማዊ የባህርና የአየር ለውጥ ሁኔታዎች ጋር የተሣሣሰረ በመሆኑ ፣ ተጽእኖው የቅርብም የሩቅም ሊሆን ይችላል። ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ፣ ብርቱ ዝንም ነው ሲጥል የከረመው? መንስዔው ምን ይሆን ?በአመዛኙ ወቅቱን

https://p.dw.com/p/19UJZ
ምስል AP

የጠበቀ ዝናም ከሚያገኙት ሃገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት። 80 ከመቶ የሚሆነው በግብርና የሚተዳደረው ህዝቧ ፣ ወንዞችን እየጠለፈ የተለያዩ እዝርእትን ከመዝራትና አትክልቶችን ከመትከል ይልቅ ከሰማይ በሚወርድ ዝናም ሲመካ የኖረበት አንዱ ምክንያትም ፣ ከሥነ ቴክኒክ ዕውቀት ማነስና የገንዘብ አቅም ከማጣት ሌላ እምብዛም የወቅቶች መዛባት ባላማጋጠሙ ሊሆን ይችላል።

ኢትዮጵያ፤ በያመቱ ፤ በተለይ እኛ ክረምት በምንለው ወቅት ፣ ከሰኔ እስከ ጳጉሜም ሆነ መስከረም የምታገኘውን ያህል ምድሯን የሚያርስ ዝናም ባታጣም የዘንድሮው መጠኑ በዛ ያለ መሆኑ ተስተውሏል። አርሶ-አደሩንም ሆነ እኽል ሸማቹን እሰየው የሚያሰኝ መሆኑን አንጠራጠርም። ይኸው በዛ ያለ ዝናም ፣ በተወሰኑ ዓመታት ወይም ጊዜያት በዑደታዊ መልኩ የሚያጋጥም ወይስ በተናጠል የሚታይ ጉዳይ ነው? የዘንድሮውን መጠነ ሰፊ የክረምት ዝናም መነሻ በማድረግ አንድ ባለሙያ አነጋግረናል ።

Regenzeit im Kongo
ምስል Bundeswehr

እርሳቸውም በኢትዮጵያ ብሔራዊው የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት (ኤጀንሲ)የአየር ጠባይ (ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ቅድመ- ማስጠንቀቂያ -የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ ፤ (ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር ) አቶ ድሪባ ቆሪቻ ናቸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ዝናብ ሲጥል መክረሙን በውጭ የምንኖር ሰዎችም በተደጋጋሚ ሰምተናል፤

የዘንድሮው ካለፉት ጋር ሲነጻጸር የሚባለውን እስከምን የሚያረጋግጥ ነው? በተለያዩ የዓመት ወቅቶች ከሚከሠቱ የተለመዱ የአየር ጠባዮች ጋር በማያያዝ አቶ ድሪባ እንዲህ ይላሉ---

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ