1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘጋቢ ፊልም ፌስቲቫል በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ሰኔ 5 2007

ዘጋቢ ፊልሞቹ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ናቸው ።የፊልም ፊስቲቫሉ በአዲስ አበባ በቅርስ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በሃገር ፍቅር፣ በብሪቲሽ ካውንስልና በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ እንዲሁም በናዝሬት ፣በመቀሌ፣ በድሬዳዋና በአዋሳም ይካሄዳል ።

https://p.dw.com/p/1FgOY
Äthiopien Festival Dokumentarfilm
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

ኢኒሽየቲቭ አፍሪቃ አዲስ ኢንተርናሽናል የተባለው የፊልም ፌስቲቫል ዛሬ ማምሻውን ጀምሮ ለአምስት ቀናት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ይካሄዳል።በዚሁ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ዝና ያተሩፉ 50 ምርጥ ዘጋቢ ፊልሞች እንደሚቀርቡ አዘጋጆች ተናግረዋል ። ዘጋቢ ፊልሞቹ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ናቸው ።የፊልም ፊስቲቫሉ በአዲስ አበባ በቅርስ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በሃገር ፍቅር፣ በብሪቲሽ ካውንስልና በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ እንዲሁም በናዝሬት ፣በመቀሌ፣ በድሬዳዋና በአዋሳም ይካሄዳል ። አዘጋጆቹ ስለ ፌስቲቫሉ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ