1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዚምባብዌ ሴቶች ከፖሊስ የገጠማቸው እንግልት

ዓርብ፣ ሐምሌ 27 2004

በዚምባብዌ መዲና ሀራሬ ካለፉት በርካታ ሣምንታት ወዲህ ከመሸ በኋላ በመንገድ ሲሄዱ የሚገኙ ሴቶች የመታሰር ዕጣ እየገጠማቸው ነው። ሴቶቹ፡ ፖሊስ እንዳስታወቀው፡ ሴተኛ አዳሪ ናቸው በሚል ምክንያት የታሰሩ ሲሆን፡ ሴተኛ አዳሪነት በሀገሪቱ በሕግ የተከለከለ ነው።

https://p.dw.com/p/15igu
Demonstration von Frauen gegen die Verhaftungen der Polizei *** Wer hat das Bild gemacht/Fotograf?: Privilege Musvanhiri Wann wurde das Bild gemacht?: Juli 2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Harare, Simbabwe
ምስል privi(c)2012

ችግሩ ግን የታሰሩት ሴቶች ሴተኛ አዳሪ አለመሆናቸው ነው። ሴቶቹ በዚሁ የፖሊስ ርምጃ አንጻር የአደባባይ ተቃውሞ ጀምረዋል። ይኸው ተቃውሞ የተለያዩ የሀገሪቱ የሴቶች መብት ተሟጋች ድርጅቶችንም ድጋፋ አግኝቶዋል።

በመቶ የሚቆጠሩ ሴቶች በሀራሬ የዩኒየን አደባባይ በመውጣት የዚምባብዌ ሴቶች በወቅቱ ከፖሊስ እየደረሰባቸው ያለውን በደል መቃወም ጀምረዋል። ታዋቂዋ ደራሲ እና የመብት ተሟጋች ቲሲቲሲ ዳንጋሬምብጋ አንዷ ናቸው። ቲሲቲሲ ዳንጋሬምብጋም በፖሊስ ታስረው ነበር።
« ይህ ፖሊስ በአሁኑ ጊዜ በሴቶች ላይ እየፈፀመው ባለው ሕገ ወጡና የኡዘፈቀደ እሥራት አንጻር የተደረገ ርምጃ ነው። ሴቶቹ በዝሙት ተግባር ተሰማርተዋል በሚል ምክንያት ፖሊስ ሴቶቹ ዕለታዊ ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ መሠረታዊውን የመንቀሳቀስ ነፃነታቸውን ገድቦዋል። አሁን እዚህ ተቃውሞ ከወጡት ሴቶች መካከል ብዙዎቹ ታስረዋል፤ ፖሊስ አጉላልቶዋቸውል። በዚህም የተነሳ ርምጃ ለመውሰድ ወስነናል። »
የሀያ ስምንት ዓመቷ አና ሜኪም አንድ ቀን ማታ ከጓደኞችዋ ጋ አምሽታ ወደቤትዋ ስትመለስ ሳለ ታስራ ነበር።
« ፖሊሶቹ ጥሩ ሴቶች ማታ ከቤታቸው እንደማይወጡ፡ ሴተኛ አዳሪዎች ብቻ ከመሸ በኋላ እንደሚወጡ ደጋግመው ነበር የነገሩን። ባሎቻችን የት እንዳሉም ጠይቁን፤ እና ባለትዳር አለመሆናችንን ስንነግራቸው፡ እንደ ትልቅ ችግር ተመለከቱት። ትያቄ ሲበዛብን መልስ ያለመስጠት መብታችን ለመጠቀም ወሰን። ይህም አስቆጣቸው። ከዚያ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደሚለቁን ነገሩን። »
ፖሊስ ሴቶቹን ማሰሩ ብቻ ሳይሆን በሀሰት ሴተኛ አዳሪ ናቸው ባለበት መሠረተ ቢስ ክስ፡ እና ወንዶችን ትቶ ሴቶችን ብቻ እየለየ በሚያስርበት ድርጊቱ ድርብ በደል እንደሚፈፅምባቸው አስታውቀዋል። የፖሊስ ኃላፊ ኢንስፔክተር ጄምስ ሳባው ወቀሳውን አስተባብለዋል። ሀራሬ ውስጥ ሴተኛ አዳሪዎች የሚያዘወትሩዋቸውን ቦታዎች እያወቁ ወደነዚህ ስፍራዎች የሚሄዱ ሴቶች ለሳቸው እንደ ሴተኛ አዳሪ እንደሚቆጥሩዋቸው ገልጸዋል።
« በየመንገዱ ቆሞ እንደ ሴተኛ አዳሪ መስራት በሕግ የተከለከለ ነው። በቀን ሴተኛ አዳሪ ነሽ ተብላ የታሰረች ሴት የለችም። የዝሙት ተግባር ይካሄድባቸዋል የተባሉ ቦታዎች አሉ፤ ያሰርናቸውም በነዚህ ቦታዎች የተገኙትን ሴቶች ነው ። እና እኛ ዒላማ ያደረግነው እነዚህን ስፍራዎች ነው። »
ፖሊስ የሚከተለው መሠረታዊ መብታቸውን በሚረግጠው በዚሁ አሰራሩ ሰበብ ብዙ ሴቶች የመታሰር ዕጣ እንዳይገጥማቸው በመስጋት ከመሸ በኋላ መውጣት እንደማይደፍሩ አደባባይ የወጡት የመብት ተሟጋጭ ሲሲ ዳናጋረምባ በመግለፅ፡ ይህን ጩኸታቸውን እስካሁን አንድም ፖለቲካኛ መልስ ባይሰጣቸውም ተቃውሞአቸውን ማሰማት እንደሚቀትሉ አስታውቀዋል።

ኬrርስቲን ፖፔንዲክ/አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ

Demonstration von Frauen gegen die Verhaftungen der Polizei *** Wer hat das Bild gemacht/Fotograf?: Privilege Musvanhiri Wann wurde das Bild gemacht?: Juli 2012 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Harare, Simbabwe
ምስል privi(c)2012