የዚምባብዌ ብሄራዊ የአንድነት መንግስት ምስረታ4 የካቲት 2001ረቡዕ፣ የካቲት 4 2001የዚምባብዌ ተቃዋሚ ፓርቲ የኤም.ዲ.ሲ መሪ ሞርጋን ቻንጋራይ የዚምባብዌ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ዛሬ ቃለ መሀላ ፈፅመዋል ።https://p.dw.com/p/GrpBምስል APማስታወቂያበስልጣን ክፍፍሉ ዛኑ ፒ ኤፍ ዋና ዋናዎቹን የስልጣን መንበሮች ይይዛል። ሁለቱ ወገኖች ባለፈዉ መስከረም ብሄራዊ የአንድነት መንግስት ለመመስረት የተመፈራረሙትን ገቢር ማድረጋቸዉ የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል ባልደረባ ሉድገር ሻዶምስኪ በፃፈዉ ሃተታ እንደጠቆመዉ የዚምባቡዌን ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ ቀዉስ ለማስወገድ እንደበጎ ጅምር የሚታይ ነዉ።