ጀርመን የየመንን ተፋላሚዎችን ለውይይት ጋብዛለች
ረቡዕ፣ ግንቦት 9 2009ማስታወቂያ
ዳግኸር በተለይ ከጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚግማር ጋብሪየል ጋር ባደረጉት ውይይት የመንን የሚያወድመውን ጦርነት በሰላም ማቆም ስለሚቻልበት ስልት መክረዋል፡፡ ጀርመን የየመን ተፋላሚዎችን ለመሸምገል በሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዕርዳታ እንደምታደርግ የጀርመኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዉይይቱ ወቅት ቃል ገብተዋል፡፡ የየመኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ከጀርመን ባለስልጣናት ጋር ስላደረጉት ውይይት የበርሊን ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤል በስልክ ማብራሪያ ሰጥቶናል፡፡ ዝርዝሩን የድምጽ መስፈንጠሪያውን በመጫን ያድምጡ፡፡
ይልማ ኃይለሚካኤል
ተስፋለም ወልደየስ
ነጋሽ መሐመድ