1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየመኑ ጦርነትና የኢትዮጵያ መንግሥት አቋም፤

ዓርብ፣ መጋቢት 25 2007

የመን ውስጥ ጠንካራ ሆኖ በተገኘው የሁቲ አማጽያን ድርጅት ላይ ፣ በስዑዲ ዐረቢያ መሪነት የአየር ኃይል ድብደባው እንደቀጠለ ነው። ጥቃቱ በማየሉም ሁቲ አምጽያንና ተባባሪዎቻቸው ከአድን የወደብ ከተማ ማዕከል አፈግፍገዋል።

https://p.dw.com/p/1F2Wi
Yemen Militär Panzer
ምስል Getty Images

ሶሪያ፤ ኢራቅና ሊባኖስ ውስጥ በሱኒ ስዑዲ ዐረቢያና በሺዓ ኢራን መካከል ሲካሄድ የቆየው የውክልና ጦርነት ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመን ላይ ስዑዲ ዐረቢያ በቀጥታ በተሣተፈችበት ሁኔታ ተከሥቷል። ስዑዲና ተጓዳኞቿ በመውሰድ ላይ ባሉት የአየር ድብደባና በሁቲዎች እንዲሁም በተባባሪዎቻቸው የመካላከል ውጊያ ወታደራዊ ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ሲብሎች ተገድለዋል ፤ ቆስለዋል። የውጭ መንግሥታት የሚሲዮን ጣቢያዎችም የውጊያው ሰለባ የመሆን መጥፎ ዕጣ ሳይገጥማቸው አልቀረም። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለምሳሌ ያህል ዒላማ ቢደረግም በሰው ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ፤ የሚሲዮኑ ሠራተኞችም እንደገና ሥራቸውን መጀመራቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ