1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሩሲያ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ከሐገሯ እንዲወጡ አዝዛለች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 25 2009

ሩሲያ፤ የዩናይትድ ስቴትስን አዲስ እርምጃ ለመበቀል 750 የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችን ከሐገሯ እንዲወጡ አዝዛለች። ከሩሲያ በተጨማሪ በሰሜን ኮሪያና በኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቀዉ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ ከየሐገራቱ ጋር የሚሠሩ የአዉሮጳ ኩባንዮችንም ሥራ የሚያጉል ነዉ።

https://p.dw.com/p/2hW3N
Donald Trump und Wladimir Putin
ምስል picture alliance/A. Lohr-Jones/A. Astafyev/CNP POOL/Sputnik/dpa

ዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ የገጠሙት የማዕቀብና የዲፕሎማሲ መበቃቀል ከሁለቱ ሐገራት ጋር የንግድ ልዉዉጥ የሚያደርጉ ሌሎች ሐገራትን  እንደሚጎዳ የፖለቲካ ተንታኞች አስታወቁ። ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንድትጥል የሚጠይቅ ሕግ የሐገሪቱ ምክር ቤት ባለፈዉ ሳምንት አፅድቋል። ሕጉ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሲፈርሙት ገቢር ይሆናል ተብሏል። ሩሲያ፤ የዩናይትድ ስቴትስን አዲስ እርምጃ ለመበቀል 750 የዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶችን ከሐገሯ እንዲወጡ አዝዛለች። ከሩሲያ በተጨማሪ በሰሜን ኮሪያና በኢራን ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል የሚጠይቀዉ የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ ከየሐገራቱ ጋር የሚሠሩ የአዉሮጳ ኩባንዮችንም ሥራ የሚያጉል ነዉ። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ