1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ በረዶ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 30 2006

በረዶ።ቅዝቃዜዉ ያዩ እንዳሉት አጥንት ይሰብራል-የሚባል ዓይነት ብቻ አይደለም፥ የአንዳድ ከተሞች ነዋሪዎች እንደሚሉት ብርድና በረዶዉ ብረቶችን ከማቀዝቀዝ አልፎ-እንደ እሳት ይፋጃል

https://p.dw.com/p/1An8U
ምስል Dan Herber

ዩናይትድ ስቴትስ፥ በአብዛኛ ግዛቶቿ አዉሮፕላኖች አይበሩም።አዉቶቡሶች አይሸከረከሩም።ትምሕርት ቤቶች አያስተምሩም።ሥራም ባብዛኛዉ የለም።አዉሮፕላን ማረፊያዎች፥ አዉራ-መንገዶች፥ የትምሕርት ቤቶች ሜዳዎች አንድ ነገር ተከምሮባቸዋል።በረዶ።ቅዝቃዜዉ ያዩ እንዳሉት አጥንት ይሰብራል-የሚባል ዓይነት ብቻ አይደለም፥ የአንዳድ ከተሞች ነዋሪዎች እንደሚሉት ብርድና በረዶዉ ብረቶችን ከማቀዝቀዝ አልፎ-እንደ እሳት ይፋጃል።እስካሁን አስራ-ስድስት ሞቷል።የዋሽግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ