1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ እስቴትስ ተዋጊ ጦር ከኢራቅ ነቅሎ መውጣቱ፣

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 25 2002

ወደ ኢራቅ በመዝመት በዚያ ሠፍሮ የቆየው የአሜሪካ ጦር ኃይል አገሪቱን ለቆ በመዉጣት ላይ ነዉ። ከተዋጊው ጦር ኃይል የመጨረሻው ክፍል፤ እስከዛሬ በተሰጠው የመጨረሻ የጊዜ ሰሌዳ አብዛኛው በዚህ ወር መዉጣቱ ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/P19H
ምስል AP

ቀሪዉ 50 ሺህ ወታደር ደግሞ ከመስከረም ወር ጀምሮ ለኢራቅ ጸጥታ አስከባሪ ሃይል ስልጠና መስጠት እና ማቋቋም ይጀምራል። ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፤ ዛሬ፣ የአገራቸዉ ተዋጊ ጦር ሃይል ዘመቻዉን አጠናቆ ወደ አገሩ መመለሱን ፤ ዛሬ ፤ በይፋ ያበስራሉ። ኢራቅ ፣ ከሳዳም ሁሴን ከሥልጣን መወገድ በኋላም ቢሆን፤ ሰላም አላገኘችም የዶቸ ቬለዉ Felix de Cuveland ስለ ኢራቅ የዘገበዉን፣ አዜብ ታደሰ እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።

ድምጽ ፩.

እንኳን ደስ ያላችሁ ! ስራችሁን በደንብ ተግብራችዃል! በሰላም ወደ አገራችሁ ተመልሳችሁ ከቤተሰቦቻችሁ እና ከጓደኞጫችሁ ለመገናኘት ያብቃችሁ።

በባግዳድ የአሜሪካ የጦር ሰራዊት የስንብት ስነ-ስርአት ላይ ነዉ። የአሜሪካ ጦር ሰራዊት ተልኮዉን በማጠናቀቅ ላይ ነዉ። የመጨረሻዉም የጦር ሰራዊት ከሁለት ሳምንት በፊት ነዉ አገሪቱን ለቆ የወጣዉ። በኢራቅ የቀረዉ 50 ሺህ የአሜሪካ ወታደር ያለምንም ጦር እንቅስቃሴ ለኢራቅ የጥበቃ ሃይላት በማሰልጠን ምክር በመስጠት ይቆያል። የዛሪ አንድ አመት ከመንፈቅ ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ ባደረጉት ንግግር

ድምጽ፪.

በኢራቅ ሙሉ በሙሉ ጸጥታ እስኪሰፍን ድረስ በሚል እድሜ ልካችንን በኢራቅ ጎዳና ጸጥታ ለማስከበር እንዘዋወርም። የኢራቃዉያን አንድነት እስኪያገኙ በሚልም አገሪቷ ዉስጥ መቆየት አንችልም

እግዲህ

በጦርነት የደቀቀችዉ የነዳጅ ዘይት ባለ ሃብቷ ኢራቅ በራስዋ አቅም ከገባችበት ማጥ መዉጣት አለባት። ግን ይሆን ለማድረግ አቅሙ አላት? በዚህ ጉዳይ የ አል ኩዱስ አል አራቢ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አብድል ባሪ አትዋን ብሩህ ተስፋ አይታያቸዉም

ድምጽ ፪.

በኢራቅ አልቃይዳ ዳግም ያንሰራፋል የሚል ግምት አለኝ። ኢራቅም በህግ የማይተዳደር እና ብጥብጥ የሞላበት ስርአት እየተቀየረች በመሆንዋ ምክንያት እንደ አልቃይዳ ያሉ አክራሪ እና አሸባሪ ቡድኖች ይፈጠራሉ።

ለዚህም ሰሞኑን በኢራቅ በተለያዩ ቦታዎች የደረሰዉ ፍንዳታ ተጠቃሽ ነዉ ሲል ጋዜጠኛ አትዋን ምሳሌ በመስጠት ያስረዳል። በኢራቅ ባለ ስልጣናት በወጣዉ መረጃ በሃምሌ ወር ብቻ 535 ያህል ህዝብ በደረሰ ድንገተኛ ጥቃት ህይወቱ አልፎአል። ይህን ያህል የሰዉ በጥቂት ግዜ ዉስጥ በጥቃት ሲያልፍ ከሁለት አመት ወዲህ የመጀመርያዉ እንደሆነም ተመልክቶአል። ዩናይትድ ስቴትስ ለኢራቅ የጸጥታ ጥበቃ ለፖሊስ ለወታደር ስልጠና እና ትጥቅ ከፍተኛ ገንዘብን ብታፈስም በኢራቃዉያኑ ጸጥታን ለማስፈን የሚደረገዉ እንቅስቃሴ አመርቂ ሆኖ አልተገኘም።

በቤሩት ዪንቨርስቲ ዉስጥ የፖለቲካ ምሁር የሆኑት ኢራቃዊ አገራቸዉ ያለዉ የጥበቃ ሃይል ቁጥር የትየለሌ ቢሆንም ቅሉ ችግሩ የጸጥታ አስከባሪዎቹ ለስራቸዉ ታማኝነት ማጣታቸዉ ነገሩን የኳሊት እንዲሄድ ያደርገዋል ሲሉ ያስረዳሉ። ኢራቃዉያን በእምነት በጎሳ እጅግ የተከፋፈሉ ናቸዉ በዝያ ላይ በእምነትም ሆነ በፖለቲካ የቆመዉ እያንዳንዱ ቡድን ከፍተኛ ዉስጣዊ ችግር ስላለበት በአንድነት በህግ እና በስርአት አገሪቱን መምራት ማስተዳደር አልተቻለም ነዉ።

ከስድስት ወር ግድም በፊት በኢራቅ ከተደረገዉ የምክር ቤት ምርጫ ወዲህ አገሪቷ ዳግም ችግር ላይ ወድቃለች። የትኛዉ የፖለቲካ ፓርቲ አዲሱን የአገሪቷን አመራር እንደሚመሰርት እስካሁን ግልጽ አይደለም። የኢራቅ ፖለቲከኞች ሁኔታዉን ባለማንቀሳቀሳቸዉ ህዝቡ ተማሯል። ይህን በማየት

የአሜሪካዉ ምክትል ፕሪዝደንት ጆባይደን በግላቸዉ የኢራቅ ፖለቲከኞች ዉሳኔ ላይ እንዲመጡ ግፊት ለማድረክ ሞክረዉ ነበር።

ድምጽ ፫.

እኔ በግሌ የኢራቅ መሪ ፖለቲከኞችን የህዝብ ፍላጎት ማሟሟያ ግዜዉ አሁን በመሆኑ የመንግስት ምስረታዉን እንዲያጠናቁ ግልጽ አድርጌላቸዋለሁ።

በኢራቅ የፖለቲካ መድረግ ህብረትን ለማምጣት አስቸጋሪ ይመስላል። በአገሪቷ የሚገኙት የፖለቲካ ጉዳይ መሪዎች የየግላቸዉ የዉጭ አገር ወዳጅነት መስርተዋል። ለምሳሌ የምርጫ አሸናፊ የተባሉት አላዊ ከቱርክ ከሳዉዲአረብያ ከዪናይትድ ስቴትስ ድጋፍን ሲያገኙ የሳቸዉ ተቀናቃኝ ኑሪ አልማሊኪ ደግሞ ከኢራን ከፍተኛ ድጋፍ ይቸራቸዋል። በዚህም የኢራቅ አለመረጋጋት ከፍተኛዉ ችግር ተጋፍጦ ቆምዋል።

አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

ሸዋየ ለገሠ