1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይድ ስቴትስና የሰሜን ኮሪያ ፉከራ

ዓርብ፣ ነሐሴ 5 2009

ሰሜን ኮርያ እና ዩናይትድ ስቴትስ አንዳቸዉ ሌላቸዉ ላይ ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ በጀመሩት ዛቻ ገፍተዋል። ፒዮንግያንግ የአሜሪካኗን ጉዋም ግዛት ለመምታት የሚያስችላልትን ቦለስቲክ ሚሳኤል ማዘጋጀቷን ስትናገር፤ ዋሽንግተን በፋንታዋ ለሰሜን ኮርያ የደገሰችዉ መሣሪያ በተጠንቀቅ እንደሚገኝ አስታዉቃለች።

https://p.dw.com/p/2i5UH
Karikatur Trump und Kim (USA Nordkorea Atomstreit)

የሰሜን ኮሪያና የአሜሪካ መዛዛት

 ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፒዮንግያንግ በጅልነት የምትለዉን አሜሪካን ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ብትሞክር ወታደራዊ መፍትሄዉ ሙሉ በሙሉ መዘጋጀቱን በትዊተር መልዕክታቸዉ ጠቁመዋል። የአሜሪካን የመከላከያ ሚኒስትር ጀምስ ማቲስ በበኩላቸዉ ምንም እንኳን የእሳቸዉ ኃላፊነት ወታደራዊ ተልዕኮዉን ማስፈፀም ቢሆንም ቀዉሱን በዲፕሎማሲ መፍታት ይቻላል የሚል ተስፋቸዉ እንዳልተማጠጠ ተናግረዋል። የቃላት ጦርነቱ እየናረ በሄደበት በዚህ ወቅት ሰሜን ኮርያ አራት ሚሳኤሎችን ወደ አሜሪካኗ ጉዋም ግዛት ለመተኮስ ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ እያለች ነዉ። በጉዋም የባህር ዳርቻ የሚገኙ ነዋሪዎች ይህን ዜና ከሰሙ በኋላ አስተያየታቸዉን እንዲህ ሰጥተዋል፤

Nordkorea Kim Jong-Un beobachtet Raketentest
ምስል Getty Images/AFP/STR

«እንዲህ ያለዉን ዛቻ ለምደነዋል፤ በቦምብ እንደምንመታም በየጊዜዉ እንሰማለን ግን ሆኖ አያዉቅም። አሁን ደግሞ በድጋሚ እየሰማን ነዉ። እናም ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም።»

«ሆኖ አያዉቅም፤ እናም ምን ስጋት አልገባኝም። ምናልባት ማደናቀፊያ ነገር ሊሆን ይችላል። ምናልባትም የፖለቲካ ርምጃ አይነት ይሆናል፤ ማለት፤ በዩናይትድ ስቴት እና በኮሪያ በኩል ምናልባት ትኩረት ለማግኘት የመፈለግ አይነት ይሆናል።»

ሚሳኤል ያነጣጠረባት የጉዋም ነዋሪዎች ጉዳዩን አቅልለዉ ቢያዩትም፤ የተለያዩ የምዕራብ ሃገራት መሪዎች ግን ወታደራዊዉ ዛቻ ስጋት የፈጠረባቸዉ መስሏል። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የተካረረዉን ዉጥረት በጦር መሣሪያ መፍታት እንደማይቻል ሲያሳስቡ፤ ሩሲያ በበኩሏ እሰጥ አገባዉ ከመጠን ማለፉን በመጥቀስ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ወደቀልባቸዉ እንዲመለሱ ጠይቃለች።

Donald Trump
ምስል Picture-Alliance/AP Photo/E. Vucci

የፖለቲካ ተንታኞች ግን የሁለቱ ሐገራት መሪዎች አንዱ ሌላዉን ከማስፈራራት አልፈዉ ዉጊያ መግጠማቸዉን ይጠራጠራሉ። አንድ ኢትዮጵያዊ የሕግ ምሑር በበኩላቸዉ ሰሜን ኮሪያ ዉጊያ ከጀመረች ከፍተኛ ጥፋት ይደርስባታል።» ይላሉ። ይሁንና ያሁኑ ዉጥረት የኑክሌር ቦምብ ዉጊያ ማስከተሉን ይጠራጠራሉ። የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ