1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ ዴሞክራቶች ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች የመጀመሪያ ክርክር

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2008

በላስ ቬጋስ ከተማ በተካሄደው በትናንቱ ክርክር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ምጣኔ ሃብት፣ የክሊንተን አወዛጋቢ ኤሜል፣ የስደተኞች ጉዳይ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር፣ የዘር መድልዎና የአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛዎቹ የክርክር ነጥቦች ነበሩ

https://p.dw.com/p/1GoTS
USA Wahlkampf Demokraten Sanders Clinton
ምስል picture-alliance/Landov

[No title]

በጎርጎሮሳዊው 2016 ለሚካሄደው የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከዴሞክራት ፓርቲ በእጩነት ለመወዳደር የቀረቡ አምስት ዴሞክራት ፖለቲከኞች ትናንት ባካሄዱት የመጀመሪያው ክርክር በምርጫ ወቅት የሚያተኩሩባቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች አሳወቁ። በላስ ቬጋስ ከተማ በተካሄደው በትናንቱ ክርክር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ ምጣኔ ሃብት፣ የክሊንተን አወዛጋቢ ኤሜል፣ የስደተኞች ጉዳይ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር፣ የዘር መድልዎና የአየር ንብረት ለውጥ ዋነኛዎቹ የክርክር ነጥቦች ነበሩ። ከ2 ሰዓታት በላይ በወሰደው በዚህ የፖለቲካ ክርክር የተሳፉት የሮድ አይላንድ አገረ ገዥ ሊንከን ቼፍ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን የቀድሞ የሜሪላንድ ሃገረ ገዥ ማርቲን ኦማሊ፣ የቬርሞንት ግዛት ሴናተር በርኒ ሳንደርስ እንዲሁም የቀድሞ የቨርጂንያ ግዛት ሴናተር ጂም ዌብ ናቸው ።

ናትናኤል ወልዴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ