1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኤስ ፕሬዚደንታዊ እጩዎች ምርጫ በአዮዋ ግዛት

ማክሰኞ፣ ጥር 24 2008

የአዮዋ ግዛት መራጮች በዩኤስ አሜሪካ የፊታችን ህዳር፣ 2016 ዓም ለሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚቀርቡትን የሬፓብሊካን እና የዴሞክራቶቹ ፓርቲዎችን እጩዎች ትናንት መረጡ።

https://p.dw.com/p/1HoCg
Infografik Iowa Vorwahl 2016 Englisch

[No title]

በዚሁ ከዩኤስ አሜሪካ ግዛቶች ሁሉ ቀድሞ የመጀመሪያውን ምርጫ ባካሄደው ግዛት ውስጥ ከሬፓብሊካውያኑ ፓርቲ የቴክሳሱ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ ቴድ ክሩዝ ሲያሸንፉ፣ ያሸነፋሉ ተብለው ተገምተው የነበሩት ቢልዮኔሩ ባለተቋም ዶናልድ ትራምፕ ሳይቀናቸው ቀርተዋል። ከዴሞክራቶቹ ፓርቲ እጩዎች ደግሞ የቀድሞ የዩኤስ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂለሪ ክሊንተን ጠንካራ ተፎካካሪያቸውን የቬርሞንትየሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ በርኒ ሳንደርስን በጠባብ የድምፅ ብልጫ ማሸነፋቸው ተገልጾዋል።

ናትናኤል ወልዴ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ