1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩክሬኑ ተቃውሞ

ረቡዕ፣ ኅዳር 25 2006

የዩክሬን መንግሥት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ልዩ የንግድና የፖለቲካ ትብብር ውል ላለመፈረም በመወሰኑ የተነሳው ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በዋና ከተማይቱ በክዬቭና በሌሎችም ከተሞች አደባባይ የወጡ ተቃዋሚዎች የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪችና መንግሥታቸው ሥልጣን እንዲለቁ መጠየቃቸውን ቀጥለዋል።

https://p.dw.com/p/1AT5L
ምስል Roman Chernomaz

መንግሥት በበኩሉ ተቃዋሚዎች ፖለቲካዊ ውጥረቱን ማባባሱን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርቧል።
ዩክሬን ውስጥ ተቃዋሚዎች አሁንም አዲስ መንግሥት እንዲመሰርት ባቀረቡት ጥያቄ ፀንተው እንደቀጠሉ ነው ። ሃገሪቱ ወደፊት ከአውሮፓ ህብርት ጋር እንድትቀላቀል የሚሹት እነዚሁ ወገኖች ወደ ውህደቱ የሚደረገው ጉዞ ያለ ፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች መሆን አለበት የሚለውን ጥሪያቸውን በዋና ከተማይቱ ክየቭ ከሚገኘው ማድያን ከተባለው የነፃነት አደባባይ አንስቶ በሌሎችም ከተሞች እያስተጋቡ ነው ። ተቃዋሚዎቹ እንደሚሉት የጀመሩት ትግል በአጭር ጊዜ ውጤት ያመጣል ብለው አይጠብቁም ። ሆኖም አደባባይ ከወጡት ሰልፈኞች አንዱ እንደሚለው ያሰቡት እንደሚሳካ አይጠራጠሩም ።
« ራዕያችንን ማሳኪያው መንገድ ረዥም ነው ። በመንገድም ላይ ችግሮች አሉ ። ርግጥ ነው ሁሉንም ወዲያውኑ አናገኝም ። እኛ እዚህ የቆምነው ለልጆቻችን ና ለልጅ ልጆቻችን የወደፊት ህይወት ነው ። እንደምናሳካውም አምናለሁ ። »
የዩክሬን መንግሥት ከአውሮፓ ህብረት ጋር የፖለቲካና የንግድ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ አለመሆኑን ባለፈው ሳምንት ከገለፀ በኋላ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ቅዳሜና እሁድ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል ። በዋና ከተማይቱ በክየቭ

Ukraine Antiregierungsprotest in Kiew 4. Dezember
ፀረ/መንግሥት ሰልፍ በዩክሬይንምስል Reuters

ተቃዋሚዎች የማድያንን አደባባይ አጥረው በቁጥጥራቸው ሥር ካደረጉ ወዲህ ግን ፀጥታ አስከባሪዎች በአካባቢው አይታዩም ። ተቃዋሚዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በኃይል የመያዝና ወደ ዚያም የሚወስዱ መንገዶችን የመዝጋት ሙከራቸውን አሁንም አላቆሙም ። መንግሥት ግን ይህ ማብቃት አለበት ሲል እያሳሰበ ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኮላ አሳሮቭ
«እርምጃዎች በሙሉ መወሰድ ያለባቸው በህገ መንግሥቱ መሠረት ነው። ስለዚህ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን በኃይል መያዝ መቆም አለበት ። የአስተዳደር ሥራዎችን ማሰናከልን ማቆም አለባቸው ።» የፕሬዝዳንት ቪክቶር ያኑኮቪች መንግሥት እንደሚለው ከአውሮፓ ህብረት ጋር ልዩ የፖለቲካና የንግድ ትብብር ውል ላለመፈረም የደረሰበት ውሳኔ ከህብረቱ ጋር መዋሃድን ያለመፈለግ ምልክት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ። በጠቅላይ ሚኒስትር ምይኮላ አዛሮቭ አባባል መንግሥት አሁን ይህን እርምጃ የወሰደው ውሉ ከመፈረሙ በፊት ፋታ ለማግኘት ነው ። ይሁንና ታዋቂውን የዓለም የቦክስ ሻምፕዮን ቪታሊ ክልችኮን ጨምሮ የዩክሬን የተቃዋሚ ወገን መሪዎች መንግሥት ለዓመታት ከተካሄዱ ድርድሮች በኋላ ውሉን አልፈርምም በማለት ህዝቡን ከድቷል ሲሉ ይከሳሉ ። ተቃዋሚው ክሊችኮ ድል እስኪገኝ ትግሉ አይቆምም ይላል ።
« ካለትግል ድል እንደማይገኝ ከማንም በላይ አውቃለሁ ። ለዚህም ነው ለድል የምንታገለው ። ለዚህም እርግጠኛ ነኝ ። ዩክሬይን ለዘላለም ትኑር ። »
ተቃዋሚዎች ከፍተኛ ጫና የፈጠሩበት መንግሥት ለተቃውሞው መነሻ የሆነውን የንግድና የፖለቲካ ውል ንግግር ለመጀመር በሚቻልበት መንገድ ላይ ልዑካኑን ወደ አውሮፓ ህብረት መቀመጫ ወደ ብራሰልስ እንዲሁም በተመሳሳይ ጊዜ በጉዳዩ ላይ የሚመክር ሌላ የልዑካን ቡድን ወደ ሞስኮ እንደሚልክ ዛሬ አስታውቋል።የዩክሬን መንግሥት ፍላጎት ከሞስኮና ከብራሰልስ ጋር የሶስትዮሽ ንግግር ማካሄድ ነው ። ይህ ግን በአውሮፓ ህብረት በኩል ተቀባይነት አላገኘም ። የአውሮፓ ህብረት ዩክሬን ከውሉ ራሷን እንድታገል ሩስያ ግፊት ታደርጋለች ሲል ይከሳል ። ያም ሆኖ የአውሮፓ ህብረት ንግግሩን እንደገና ለመጀመር ፈቃደኛ መሆኑን አስታውቋል ። ተቃዋሚዎች እንደሚሉት መንግሥት ሥልጣን ለቆ ወቅቱን ያልጠበቀ ፕሬዝዳንታዊና ምክር ቤታዊ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ተቃውሞአቸው አይቆምም ።

Ukraine Vertrauensabstimmung Klitschko 03.12.2013
ቪታሊ ክሊችኮምስል Reuters

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ