1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩጋንዳ አጠቃላይ ምርጫ

ሐሙስ፣ የካቲት 10 2008

ዩጋንዳዉያን ዛሬ በሀገራቸዉ በሚካሄደዉ ፕሬዝደንታዊ እና ምክር ቤታዊ ምርጫ ድምፃቸዉን ሲሰጡ ዉለዋል። ቀደም ብለዉ የሀገሪቱ የምርጫ አስፈፃሚ ባለስልጣናት ምርጫዉን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን አስፈላጊዉን ዝግጅት አድርገናል፤ የምርጫ ቁሳቁስም ወደሚፈለግበት አድርሰናል የሚል መግለጫ ሰጥተዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/1HxV9
Uganda Kirihura Präsidentschaftswahlen Wahllokal Wähler
ምስል Reuters/J. Akena

[No title]

ሆኖም ዛሬ በዋና ከተማ ካምፓላ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቶችና አስፈላጊ ቁሳቁሶች አልቀረቡም ተብሎ ድምጽ መስጠት የሚጀመርበት ጊዜ በሰዓታት መጓተቱ ተሰምቷል። በዚህ ምክንያትም ግጭት መቀስቀሱም ተነግሯል። ዩጋንዳዉያን አስከፊ አገዛዞችን አሳልፈዉ ስልጣን ላይ የወጡት የ71ዓመቱ ዩዌሪ ሙሴቪኒ ለመጪዎቹ ዓመታትም በመንበራቸዉ ላይ ሊሰነብቱ እንደሚችሉ የሚገምቱ ብዙዎች ናቸዉ። አብዛኛዉ ከከተማ ክልል ዉጭ የሚኖር ዜጋ ደጋፊያቸዉ እንደሆነ ይነገራል። ላለፉት ተከታታይ አራት ምርጫዎች እሳቸዉን በመፎካከር ለምርጫ የቀረቡት የቀድሞ ሃኪማቸዉ ኪዛ ቤሲጄ ደጋፊዎች በከተሞች በተለይም ካምፓላ ዉስጥ እንደሚበረክቱ ነዉ ዘገባዎች የሚያሳዩት። የድምፅ ቆጠራዉ ማምሻዉን ይጀምራል ተብሎ ስለሚጠበቀዉ የዩጋንዳ የምርጫ ዉሎ ናይሮቢ ከሚገኘዉ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ጋር በአጭሩ ተወያይተናል። ፋሲል ዛሬ ስለነበረዉ የምርጫ ሁኔታ በማብራራት ይጀምራል።

ሸዋዬ ለገሠ

ፋሲል ግርማ

ኂሩት መለሰ