1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደርግ ዘመን ባለሥልጣናት መፈታት

ረቡዕ፣ መስከረም 24 2004

በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው 23 ባለሥልጣናት መካከል፣16 ቱ ትናንት መፈታታቸው ተገልጿል። ባለሥልጣናቱ የተፈቱት፤ በሃይማኖት ተጠሪዎች ጥረት ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/RpJO
በደርግ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው በከፊልምስል AP

ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፤ «የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል » ብሎ የከሠሣቸው በደርግ የአገዛዝ ዘመን ከፍተኛ ኀላፊነት ከነበራቸው 23 ባለሥልጣናት መካከል፣16 ቱ ትናንት መፈታታቸው ተገልጿል። ባለሥልጣናቱ የተፈቱት፤ በሃይማኖት ተጠሪዎች ጥረት ነው ተብሏል። የሃይማኖት ሰዎች፤ ከወዲሁ፤ ፍትኅና ርትእ እንዲኖር፤ ትኩረት ሰጥተው መሥራት፤ ሰዎች አላግባብ፤ በግፍ እርምጃ እንዳይታሠሩ ፤ እንዳይገደሉ፤ ማስተማር፤ ዕርቀ-ሰላም እንዲወርድ መጣር ፤ መንፈሳዊ ተልእኮአቸው እንደሚያስገድዳቸው የታወቀ ነው። 20 ዓመት በእሥራት ላይ ከቆዩ በኋላ፤ ስለተፈቱት የደርግ ባለሥልጣናት ፤ ታደሰ እንግዳው የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ