1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳኑ የጎሳ ግጭትና የአቢየ ጉዳይ

ሰኞ፣ ጥር 7 2004

በደቡብ ሱዳንዋ የጆንግሌ ግዛት በተባባሰው የጎሳ ግጭት ሰበብ የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር እያጨመረ ሄዷል ። መንግሥት እንዳስታወቀው ባለፈው ቅዳሜ እኩለ ለሊት ላይ 13 ሰዎች ሲገደሉ አራት ደግሞ ቆስለዋል ።

https://p.dw.com/p/13kai
በፒቦር ፣ ደቡብ ሱዳን ፤ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፣ምስል dapd

በከብት ዝርፍያ ምክንያት በሉ ኑዌርና በመርሊ ጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ባለፈው ሳምንት ብቻ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 100  እንደሚጠጋ መንግስት አስታውቋል ። በግጭቱ ወደ 60 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ መጎዳቱም ተዘግቧል ። በሌላም በኩል ሱዳንንና ደቡብ ሱዳንን የሚያወዛግበው የአቢየ ግዛት ጉዳይ እስካሁን እልባት አላገኘም ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይልጊዮርጊስ  ስለ ጆንግሌው የጎሳ ግጭት ና ስለ አወዛጋቢው የአቢየ ግዛት በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን እና በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደሮችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል ።
 

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ሒሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ