1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን መኮንኖች የአዲስ አበባ ጉባኤ

ቅዳሜ፣ መስከረም 8 2008

የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና አማፂያን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ካለፈው ሳምንት እሁድ አንስቶ አዲስ አበባ ውስጥ ያካሄዱት የሰላም ንግግር ፤ ትናንት አርብ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል።

https://p.dw.com/p/1GZBL
Südsudan General Martin T. Kenyi
ምስል DW/T. Tedla

[No title]

የጦር መኮንኖቹ ለውይይት ከቀረቡት ሰባት ጉዳዮች በአንዱ ብቻ አለመስማማታቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል። መኮንኖቹ ያልተስማሙት ዋና ከተማይቱን ጁባን ጨምሮ የሌሎች ከተሞችን ፀጥታ በሚያስከብር ፖሊስ አወቃቀር ላይ ነው። በስምምነቱ መጨረሻ ላይ የተዘጋጀውን ውል የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ወገኖች እና ሌሎች የአማፂያን መኮንኖች ቢፈርሙም፤ ከአማፂያኑ መካከል የአንዱ ቡድን ሳይፈርም ቀርቷል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ