1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ውዝግብ እና የሲብሉ ሕዝብ ስቃይ

ማክሰኞ፣ ጥር 6 2006

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር ሠራዊት ቃል አቀባይ ከጦርነት በመሸሽ ላይ የነበሩ 200 ሰዎች መስጠማቸውን ገለጡ። የጦር ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ፊሊፕ አጉዔር፤ ነጭ ዐባይን ስታቋርጥ በሰጠመችው ጀልባ ተሣፍረው የነበሩት አብዛኞቹ ሴቶችና ሕጻናት ነበሩ።

https://p.dw.com/p/1AqQi
Flüchtlinge in Minkaman Südsudan
ምስል Reuters

በአማጽያን እጅ ከምትገኘውና ውጊያ ከተፋፋመባት ከተማ ከቦር ለመሸሽ በ 10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ከእንጨት በተሠሩ ጀልባዎች ነጭ ዓባይን ማቋረጣቸው ታውቋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግምት መሠረት ፤ ባሁኑ ጊዜ፤ 230,000 ሰዎች ከጦርነቱ በመሸሽ ላይ ናቸው። የሰላም ውይይት ከሚካሄድበት ካዲስ አበባ የአማጽያኑ ቃል አቀባይ ፣ የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ብርጋዲየር ጀኔራል ሉል ሬይ ኮንግ፣ የዩጋንዳ የጦር ሄሊኮፕተሮችና ተዋጊ ጄት አኤሮፕላኖች ፣ የአማጻያኑን ይዞታዎች ደብድበዋል ብለዋል። ሌላው መፍቀሬ አማጽያን ባለሥልጣን ፣ ጌዴዎን ጋትፕን ታዖር ፣ አማጽያኑ ተዋጊዎች፤ የሚያፍን ጭስ ባለውና በሚያቅጥል ጦር መሳሪያ ተደብድበዋል ፤ ይህም ምናልባት ነጭ «ፎስፈረስ» ሳይሆን አልቀረም ማለታቸውን AP ዜና አገልግሎት ጠቅሷል። በደቡብ ሱዳን የመንግሥቱ ጦር ኃይላት በቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቸር ዙርያ የተሰባሰቡት ዓማፅያን የያዙዋትን የመጨረሻዋን የጆንግሌይ ግዛት ዋና ከተማ ቦርን መልሰው ለመቆጣጠር ጥቃታቸውን ባጠናከሩበት ድርጊት የሲቭሉ ሕዝብ ስቃይ ተባብሶዋል።

Fähre in Minkaman Südsudan
ምስል Reuters

ተክሌ የኋላ/አድሪያን ክሪሽ /ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ