1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን የሰላም ንግግር

ማክሰኞ፣ የካቲት 4 2006

የደ/ሱዳን ኣማጺያን ከድርድሩ እራሳቸውን እንደሚያጋሉ ያስጠነቀቁት፤ ትላንት ከአዲስ ኣበባ እንደተገለጸው በሁለት ምክኒያቶች ነው። አንደኛው ያልተፈቱት አባሎቻቸው በኣስቸኩዋይ ካልተለቀቁ እና ሁለተኛው ደግሞ በዚያች ሀገር የሚገኙ የኡጋንዳ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው ካልወጡ በሚል ነበር በቀጣዩ ድርድር ላይ እንደማይካፈሉ ያስታወቁት።

https://p.dw.com/p/1B6un
Unterzeichnung Waffenstillstandabkommen für Südsudan in Addis Abeba Äthiopien 23.01.2014
ምስል picture-alliance/dpa

ከዚያ በኋላ በኢጋድ አማካኝነት በተለይም ከኢትዮጵያ በኩል በተደረገ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማለት ይቻላል ዛሬ ሁለቱም ወገኖች አዲስ አበባ ላይ አዲስ ድርድር lmጀመር ተስማምቷል። የደ/ሱዳኑ ግጭት እንደተቀጣጠለ የተያዙት ከፍተኛ የተቃውሞ ወገን መሪዎች 11 ነበሩ። ባለፈው ወር የመጀመሪያውን የሰላም ስምምነት በተፈራረሙ ማግስት ሰባቱ መለቀቃቸው ሲታወስ አራቱ ግን ኣሁንም ድረስ በጁባ እንደታሰሩ ናቸው። ኣሁን በሚጀመረረው አዲሱ ግርድር ውስጥ ዋናው ኣደራዳሪ የቀድሞው የኢትዮጵያ የው/ጉ/ሚ አምባሳደር ስዩም መስፍን እንደሚሉት የተፈቱት ሰባቱ የተቃውሞ መሪዎችም ወደ አዲስ ኣበባ ሄደው ድርድሩን እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። ይሁንና አሉ አምባሳደር ስዩም መስፍን የተፈቱት ተቃዋሚዎች ከዓማጺያኑ ጎን ላይቆሙ ይችላሉ። እናም ድርድሩ የሶስትዮሽ ሊሆን እንደሚችልም አምባሳደር ስዩም ሳይጠቅሱ ኣላለፉም።

Südsudan Rebellen 10.02.2014
ምስል Reuters

የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝም የደ/ሱዳኖች ድርድሩ እንዲጸና የተማጸኑ ሲሆን በዚያች ኣገር የሚገኘው የኡጋንዳ ጦር ግን ኣገሪቱን ለቆ መውጣት እንዳለበትም ኣሳስቧል። ጠ/ሚ/ሩ ትላንት ለዘጋቢዎች እንደነገሩት ሌሎች በጉዳዩ ውስጥ ለመግባት ፍላጎቱ ያላቸው ወገኖችም በሌላኛው ወገን ስላሉ የደ/ሱዳኑ ግጭት አካባቢያው ፈርጅ ከመያዙ በፊት የውጪ ኃይሎች እጃቸውን መሰብሰብ ይኖርባቿል።

በተያያዘ ዜና በደቡብ ሱዳን ተፈጸመ የተባለውን የጦር ወንጀል ለማጣራት መቀመጫውን ዘ ሄግ ኔዘርላንድስ ያደረገው ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎት ፍላጎት እንዳለው ኣስታውቋል። ይሁን እንጂ በዚያች ሀገር ተፈጸመ የተባለውን የጦር ወንጀል ገብቶ ለመመርመር ICC ከተመድ የጸጥታ ጥበቃው ም/ቤት ይሁንታ ማግኘት ኣለበት። አለያም በደ/ሱዳኑ መንግስት መጋበዝ ይኖርበታል። የደ/ሱዳኑ ፕሬዚደንት ሳልቫኪርም ቢሆኑ ICC መግባት ከፈለገ በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተፈጸሙ የተባሉትን የጦር ወንጀሎችም ሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ማጣራት ይችላል እያሉ ነው። ኣንዳንድ ግድያዎችን ለማጣራት የደ/ሱዳን መንግስት ከወዲሁ ኣንድ ኣጣሪ ኮሚቴ ማቋቋሙንም ኪር አስታውቐል።

Flüchtlinge Südsudan
ምስል Reuters

በዚሁ መሰረት በርካታ የሰብዓዊ መብትጥሰቶች እና በሁለቱም ወገን የጦር ወንጀል መፈጸሙን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተናገሩ ነው። ዓለም ዓቀፉ የወንጀል ችሎትም በደ/ሱዳን የተከሰተውን ቀውስ ለመመርመር ፍላጎት ኣለው። ይሁን እንጂ የICC ቃል ኣቀባይ ፈሀድ አል አብደላህ እንደሚሉት ከሆነ ICC በዚያች ሀገር ምርመራ ለማካሄድ የሚችለው በሁለት መንገድ ብቻ ነው።

ደ/ሱዳን የICC አባል አይደለችም ያሉት የ ICC ቃል አቀባይ ፈሀድ አል አብደላህ የ ተመድ የምርመራ ስልጣን ካልሰጠው ወይንም የጁባው መንግስት በራሱ ጊዜ ካልጋበዘው ICC በዚህ ጉዳይ የሚገባበት ዕድል አይኖረውም።

ካለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽ ጀምሮ በደ/ሱዳን ተቀስቅሶ በነበረው አውዳሚ ጦርነት ከ 10,000 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ 700,000 የማያንሱ ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸው ተዘግቧል። 123,400 ያህል ህዝብ ደግሞ ወደ ጎረቤት ኣገሮች መሰደዱም ታውቐል።

ጃፈር ዓሊ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ