1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳን ጥቃት እና የኢጋድ ሽምግልና

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 8 2007

መፍትሄ ያጣውን የደቡብ ሱዳን ጦርነትለማስቆም ተፋላሚ ኃይላትን ሸምጋይ የሆነው የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን- ኢጋድ ሰሞኑን ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለፈው አንድ ወር ገደማ ተፈፀመ ያለውን ጥቃትና የስምምነት ጥሰት የሚገልፅ ዘገባ አውጥቷል።

https://p.dw.com/p/1E5oy
Süd Sudan Gipfel im Präsidentenpalast von Addis Abeba
ምስል Yohannes G/Eziabhare

በደቡብ ሱዳኑ የርስ በእርስ ጦርነት እስካሁን በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ህይወት ጠፍቷል። በሚሊዮን የሚቆጠርከመኖርያቀዩተፈናቅሏል።የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን- ኢጋድ እስካሁን በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና በቀድሞዉ ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ደጋፊዎች መካከል የተጀመረዉን ጦርነት ለማስቆም ተፋላሚዎችን ቢያደራድርም ጦርነቱን ማስቆም አልቻለም።

Süd Sudan Gipfel im Präsidentenpalast von Addis Abeba
ምስል Yohannes G/Eziabhare

ኢጋድ ባወጣው ዘገባ ስምምነቱን ለማረጋገጥ ወደ አካባቢው የሄዱ የኢጋድ ታዛቢዎች አካባቢውን እንዳይጎበኙ መታገዳቸውን ይጠቁማል። ከዚህም ሌላ ጆንግሌይ እና ናሲር በተባሉት ግዛቶች ስምምነቱ ተጥሶ ግጭቶች እንደተካሄዱ ይገልፃል። በኢትዮጵያ የሰላም እና ልማት ዓለም አቀፍ ተቋም የአፍሪቃ ቀንድ ተመራማሪ የሆኑት አቶ አቤል አባተ የኢጋድ ሽምግልና መፍትሄ ያላስገኘበት ምክንያት በርካታ ናቸው ይላሉ።ኢጋድ አንድ ዓመት የሞላውን ጦርነት ለመፍታት ባደረገው ጥረት ጠንካራ ርምጃ ሊወስድ ያልቻለበት ምክንያት ደግሞ የኢጋድ መብት የተወሰነ በመሆኑ ነው ይላሉ ተመራማሪ አቤል አባተ ቢሆንም ኢጋድ ከተግዳሮቶቹ አኳያ አቅሙ የሚፈቅደውን ነገር አድርጓል ብለው አቶ አቤል ያምናሉ። አቶ አቤል ጦርነቱን ለማስቆም መፍትሄ ያሉትን እና ለሌሎችም ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተውናል። ከዚህ በታች በድምጽ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ