1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳኖች የሰላም ንግግር

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 25 2006

የማቻርና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ተደራዳሪ ልዑካኖች አዲስ አበባ ውስጥ በተናጠል ከሸምጋዩ ከምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በእንግሊዘኛው ምህፃር IGAD ጋር እየተነጋገሩ ነው ። ቀጥተኛው ወይም የፊት ለፊቱ ንግግር ደግሞ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ።

https://p.dw.com/p/1Akxg
Konflikt im Südsudan Regierungssoldaten 19.12.2013
ምስል picture-alliance/dpa

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች አዲስ አበባ ውስጥ የጀመሩትን የሰላም ንግግር በቀጠሉበት በዛሬው እለት በአማፅያንና በመንግሥት ወታደሮች መካከል ውጊያው መባባሱ ተዘግቧል ። በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሚመሩት አማፅያን ዋና ከተማይቱን ጁባ በመክበብ ላይ መሆናቸውን እንደሚናገሩ የጀርመን ዜና አገልግሎት DPA አስታውቋል ።ውጊያው በመባባሱ በጁባ የአሜሪካን ኤምባሲ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ የቆንሳላ አገልግሎቱን እንደዘጋ ነው ። የማቻርና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ተደራዳሪ ልዑካኖች አዲስ አበባ ውስጥ በተናጠል ከሸምጋዩ ከምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በእንግሊዘኛው ምህፃር IGAD ጋር እየተነጋገሩ ነው ። ቀጥተኛው ወይም የፊት ለፊቱ ንግግር ደግሞ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ። ስለእሳካሁኑ ንግግር ሂደት የአዲስ አበባውን ወኪላችንን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ጌታቸው ተድላ

ኂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ