1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃው የስራ ማቆም አድማ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2002

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች ትናንት የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ዛሬም ቀጥሏል ።

https://p.dw.com/p/OrfY
ምስል picture-alliance / dpa

የስራ ማቆም አድማውን የጠሩት የሰራተኛ ማህበራት የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተፈፃሚ እስካልሆነ ድረስ የመንግስት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ አስጠንቅቀዋል ። ጥያቄአቸውም 8.6 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን እንዲሁም መንግስት ለመኖሪያ ቤት የሚሰጠው ድጎማ ወደ 1000 የደቡብ አፍሪቃ ራንድ ወይም ወደ 137 ዶላር ከፍ ይደረግልን የሚል ነው ። የደሞዝ ጭማሪውን ከሰባት በመቶ ፈቅ እንደማያደርግ እና ከዚህ በላይ መክፈል እንደማይችል መንግስት አስታውቋል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ