1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃ ምርጫ ውጤት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2008

ደቡብ አፍሪቃን ከ46 ዓመታት የዘር መድልዎ ስርዓት ያወጣው ኤ.ኤን.ሲ በሃገር አቀፍ ደረጃ 52 በመቶ ድጋፍ ማግኘቱ ቢገለጽም በፕሪቶርያ በጆሃንስበርግ እና በፖርት ኤሊዛቤት ከተሞች አብላጫ ድምፅ ማግኘቱ ያጠራጥራል እየተባለ ነው።

https://p.dw.com/p/1JbgG
Südafrika Kommunalwahlen
ምስል picture-alliance/AP Photo

[No title]




ትናንት በተካሄደው የደቡብ አፍሪቃ የአካባቢያዊ አስተዳደር እና የማዘጋጃ ቤቶች ምርጫ ገዥው ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት በእንግሊዘኛው ምህጻር ኤ ኤን ሲ በአራት ቁልፍ ከተሞች ሊሸነፍ እንደሚችል እየተነገረ ነው ። እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ በተካሄደ ቆጠራ ደቡብ አፍሪቃን ከ46 ዓመታት የዘር መድልዎ ስርዓት ያወጣው ኤ.ኤን.ሲ በሃገር አቀፍ ደረጃ 52 በመቶ ድጋፍ ማግኘቱ ቢገለጽም በፕሪቶርያ በጆሃንስበርግ እና በፖርት ኤሊዛቤት ከተሞች አብላጫ ድምፅ ማግኘቱ ያጠራጥራል እየተባለ ነው ። 259 ማዘጋጃ ቤቶች ካሏት ከደቡብ አፍሪቃ 8 ቱ ትላልቅ ከተሞች አንዱ የሆነው ኬፕ ታውን ብቻ ነው በተቃዋሚው በዲሞክራሲያዊ ህብረት ፓርቲ የሚተዳደረው ። ስለ ደቡብ አፍሪቃ ምርጫ ውጤት እና አንድምታው የጆንሃንስበርጉ ወኪላችን መላኩ አየለን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
መላኩ አየለ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ