1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃ ፖለቲካ

ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2008

የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ለመኖሪያ ቤታቸዉ ማስዋቢያ እና ማዘመኛ ከፍተኛ የሕዝብ ገንዘብ ተጠቅመዋል የሚለዉ ወቀሳ ከቀረበባቸዉ ወዲህ በሚመሩት ሀገር ምክር ቤት ዉስጥ ሞገስ እያጡ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Iq67
Jacob Zuma Korruption Prozess
ምስል Getty Images/AFP/R. Jantilal

[No title]

በትናንትናዉ ዕለት የሀገሪቱ ምክር ቤት አባላት የእሳቸዉን ዘገባ ወይም ንግግር ላለመስማት ያሳዩት ተቃዉሞ የኃይል ርምጃን ሳይቀር አስከትሎ ታይቷል። ምክር ቤቱ ዉስጥ ቀይ ልብስ ለብሰዉ የሚታደሙት ለኤኮኖሚ ፍትህ እታገላለሁ የሚለዉ ፓርቲ አባላት ያሳዩትን ተቃዉሞ ለማስቆም የጸጥታ ኃይሎች የተከበረዉን የሕብ ተወካዮች መሰብሰቢያ አዳራሽ የድብድብ መድረክ አስመስሎታል። የሀገሪቱ ቴሌቪዥኖች በቀጥታ ያሰራጩት ይህ ትዕይንትም የደቡብ አፍሪቃ ፖለቲካ ወዴት እያመራ ነዉ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ሸዋዬ ለገሠ ይህን በሚመለከት ከጆሃንስበርግ ጋዜጠኛ መላኩ አየለን በስልክ አነጋግራለች።

መላኩ አየለ

ሸዋዬ ለገሠ