1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዱር እንስሳት ጥበቃ ጉዳይ

ቅዳሜ፣ የካቲት 8 2006

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየውን ሕገወጥየዱርእንስሳትአደንናንግድንበተመለከተ ከመላ ዓለም የተውጣጡ የመንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች እና ጠበብት በዚህ ሳምንት ለንደን ብሪታንያ ስብሰባ አካሄዱ። ለተፈጥሮ ጥበቃ እና ለዱር አራዊት ህልውና የሚሟገቱት ጠበብት እንዳመለከቱት፣

https://p.dw.com/p/1B9Wr
Symbolbild Wilderei in Simbabwe
ምስል Desmond Kwande/AFP/Getty Images

ሕገ ወጡ የዱር አራዊት ንግድ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ የተስፋፋ ሲሆን ፣ ዝሆን፣ አውራሪስ እና ነብሮችን የመሳሰሉት ዱር አራዊቶች የመጥፋት ስጋት ተደቅኖባቸዋል። በአስርሺዎችየሚቆጠሩዝሆኖችእናከሺየሚበልጡአዉራሪሶችተገድለዋል።የለንደን የዱር አራዊት ማህበር ያስተናገደው ስብሰባ ዓላማ እነዚህን የዱር አራዊት መከላከል እና ከነሱ የሚገኘውን ለምሳሌ የዝሆን ጥርስ ሕገ ወጥ ንግድን መቀነስ ነው።

« በዝሆን ጥርስ የሚደረገውን ሕገ ወጥ ንግድ ለማስቆም በጋራ አንድ መንገድ ካላገኘን በስተቀር፣ በሚቀጥሉት አስር፣ አስራ ሁለት ዓመታት በአህጉራችን አንድም ዝሆን አይገኝም።

Getöteter Elefant im Niassa-Park
ምስል E. Valoi

ከላይ የተጠቀሰውን ማስጠንቀቂያ የሰጡት በለንደኑ ስብሰባ የተካፈሉት የታንዛንያ ተወካይ አሌግዛንደር ሶንጎርዋ ናቸው። ቀጣዩ ትውልድ ዝሆን፣ አውራሪስ እና ነብሮችን ማወቅ ያለበት ከታሪክ መጽሓፍት ብቻ መሆን እንደሌለበትም በለንደኑ ስብሰባ የተካፈሉት ተወካይ በማሳሰብ፣ ጥረት ካልተደረገ አሁን በዓለም ያለው የዱር አራዊት ቁጥር በቀጣዮቹ አርባ ዓመታት ውስጥ በ90% ይቀንሳል።

ጠበብት ያሰሙት ማስጠንቀቂያ ሰሚ ጆሮ ሊያገኝ እንደሚገባ የስብሰባው ተካፋዮች ተስማምተውበታል። ምክንያቱም በአፍሪቃ ያለው የዝሆን መንጋ ባለፉት ዓመታት በጉልህ ቀንሶዋል። በጀርመን ርዳታ በ2013 ዓም የተካሄደ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በታንዛንያ የሴሉ ብሔራዊ የዱር አራዊት መጠበቂያ ሰፈር ውስጥ በ1970ኛዎቹ ዓመታት 109,000 ዝሆኖች ይገኙ ነበር፤ ዛሬ 13,084ብቻ ናቸው። በዱር አራዊቱ መጠበቂያ ሰፈር ያሉትን እንሰሳት የመቁጠሩ ተግባር ግዙፍ ስራ መጠየቁን በጀርመን የፍራንክፈርት የዱር አራዊት ማህበር ባልደረባ ክሪስቶፍ አስረድተዋል።

« በርካታ አይሮፕላኖች ለሦስት ሳምንታት ያህል በየቀኑ በዚያ በረራ አድርገዋል። በዚሁ ጊዜ 80,000 ኪሎሜትር ስፋት ባለው አካባቢ በመብረር ዝሆኖችን ቆጥረናል፣ ለቀጣይ ቁጥጥር እንዲመችም ፎቶ አንስተናል።»

Spitzmaulnashorn Kenia
ምስል Imago/Chromorange

እንደ ሶኖጎራዋ አስተያየት፣ ለጥርሳቸው ሲባል የሕገ ወጥ አዳኞች እና ነጋዴዎች ዒላማ የሆኑት ዝሆኖች ለተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ልዩ ድርሻ ያበረክታል።

« አንድ ዝሆን አንድ ዛፍ ቢገነድስ ለተፈጥሮ አካባቢ ይዞታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አያሳርፍም፣ እንዲያውም፣ ድነ ውስጥ መኖር ለማይችሉ ንዑሳን ዝንሰሳት የመኖሪያ ቦታ ነው የሚፈጥረው። »

አፍሪቃውያት ሀገራት በሚያወጡዋቸው ዘገባዎች መሠረት፣ በ2013 ዓም ከሕገ ወጥ አዳኞች እና ነጋዴዎች የበይፋ የተያዘው የዝሆን ጥርስ መጠን 42 ቶን ነበር። ለዱር አራዊት ጥበቃ የሚሟገቱ ወገኖች ይኸው በተለይ በእስያ ተፈላጊ የሆነው የዝሆን ጥርስ መጠን ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ነው ያስታወቁት። በሕገ ወጥ መንገድ ከአፍሪቃ ከሚወጣው የዝሆን ጥርስ ፣ እንዲሁም የአውራሪስ ቀንድስ መካከል ትልቁ ከፊል ወደ ቻይና ነው የሚሄደው። የመጥፋት ስጋት ከተደቀነባቸውና በደቡብ አፍሪቃ ካሉት አውራሪሶችመካከል በ2013 ዓም 1000 ተገድለዋል።

ችግሩን ለበመታገሉ ረገድ አፍሪቃውያት ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ተቀባዮቹ እስያውያት ሀገራትም ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ጀርመናዊትዋ ማርጊት ሄልቪግ ቨተ አሳስበዋል።

« በተቀባዮቹ ሀገራትም ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖር ጥረት ሊደረግ ይገባል። ግምሩክ በሕገ ወጥ መንገድ የሚዘዋወረውን የአውራሪስ ቀንድ ወይም የዝሆን ጥርስ መያዝ መቻል አለበት። በተለይም ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ መቻል አለበት። »

ታንዛንያዊው ሶንጎርዋ እና የሌሎች 50 ሀገራት አቻዎቻቸው በሕገ ወጦቹ የዱር አራዊት፣ እንዲሁም፣ የዝሆን፣ አውራሪስ፣ ወዘተ ጥርስነጋዴዎች አንፃር ሊወሰድ ስለምችል ርምጃ ከመከሩ በኋላ የቦትስዋና፣ ጋቦ፣ ቻድ እና የታንዛንያ መሪዎች ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት በዝሆን ጥርስ ላለመነገድ የወጣውን ደንብ ለማክበር ቃል ገብተዋል።

የተመድ ፀጥታ ድርጅትም በሕገ ወጡ የዱር አራዊት አደንና ንግድ አንፃር የሚታገል አንድ ቡድን አቋቁሞዋል። ይህ ርምጃ በተለይ ሕገ ወጡ ንግድ የደራባቸው ቻይና እና ታይላንድን የመሳሰሉ ሀገራት ስለተጠቃለሉበት ውጤታማ ሊሆን ይችላል ተብሎ ተገምቶዋል።

ፊሊፕ ዛንድነር/አርያም ተክሌ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ