የዲላው ጥቃት እና ጉዳት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 2 2009ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በደቡብ ክልል በሚገኘው በዲላ እና በአካባቢው ከተሞች በደረሰው ጥቃት ከተፈናቀሉት እና ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል የአካባቢው ተወላጆችም እንደሚገኙበት ተነገረ። ለንደን ነዋሪ የሆኑ አንድ የአካባቢው ተወላጅ ጥቃት አድራሾቹ በብዛት በመውጣት አዛውንት ህጻን ሴት ሳይለዩ ህይወት ማጥፋታቸውን ፣ ሰዎችን ማቁሰላቸውን እና ቤቶችን እና የተለያዩ ንብረቶችን ማቃጠላቸውን በስልክ ከቤተሰቦቻቸው አባላት እንደሰሙ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ያነጋገረቻቸው የለንደንዋ ወኪላችን ሀና ደምሴ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅታለች።
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ