1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳርፉር ግጭትና የተመድ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 24 2004

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ወደ ዳርፉር ግዛት የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲላክ ውሳኔ ካሳለፈ ዛሬ ልክ 5 አመት ደፈነ ። በምዕራብ ሱዳንዋ ግዛት በዳርፉር እጎአ ከ2003 አም አንስቶ በተለያዩ የአማፅያን ቡድኖችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው ።

https://p.dw.com/p/15hMu
UNAMID peacekeeper Sergent Kindu Tarekegn, from Adigrat, Ethiopia, escorts a family that is returning home after farming outside Gereida (South Darfur) July 25, 2012. According to UNAMID, women, children and the elderly living in camps, in the government forces controlled Gereida, usually farm surrounding lands while men work in further areas in order to avoid robberies, rapes and other perpetrations. UNAMID added that in May, the rebel movement occupied Gereida for 24 hours after a big clash that destroyed telecommunication facilities and several buildings. UNAMID has deployed a battalion of more than 800 soldiers from Ethiopia for the protection of civilians. Picture taken July 25, 2012. REUTERS/Albert Gonzalez Farran/UNAMID/Handout (SUDAN - Tags: POLITICS MILITARY AGRICULTURE CONFLICT) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
ምስል Reuters

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ወደ ዳርፉር ግዛት የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲላክ ውሳኔ ካሳለፈ ዛሬ ልክ 5 አመት ደፈነ ። በምዕራብ ሱዳንዋ ግዛት በዳርፉር እጎአ ከ2003 አም አንስቶ በተለያዩ የአማፅያን ቡድኖችና በመንግሥት ኃይሎች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው ። በዚህ ውጊያም ከ 180 ሺህ እስከ 500 ሺህ የሚደርስ ህዝብ ህይወት ሳይጠፋ እንዳልቀረና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩም እንደተፈናቀሉ ይገመታል ። ይሁንና በአሁኑ ጊዜ መገናኛ ብዙሃን ስለ ዳርፉር ግጭት እምብዛም አያወሱም ። ከዚያ ይልቅ ይበልጥ ትኩረት የሳቡት የአረቡ አለም ህዝባዊ አመፅና የደቡብ ሱዳን መገንጠል ሆነዋል ። ይሁንና የዶቼቬለው አድርያን ኪርሽ እንደዘገበው በዳርፉር ግጭቱ አሁን ቀጥሏል ፤ ሰላማዊ ሰዎችም እየተሰቃዩ ነው ።

UNAMID peacekeepers from Ethiopia prepare to go on a night patrol in an Armored Personnel Carrier (APC) in Gereida (South Darfur) July 25, 2012. According to UNAMID, women, children and the elderly living in camps, in the government forces controlled Gereida, usually farm surrounding lands while men work in further areas in order to avoid robberies, rapes and other perpetrations. UNAMID added that in May, the rebel movement occupied Gereida for 24 hours after a big clash that destroyed telecommunication facilities and several buildings. UNAMID has deployed a battalion of more than 800 soldiers from Ethiopia for the protection of civilians. Picture taken July 25, 2012. REUTERS/Albert Gonzalez Farran/UNAMID/Handout (SUDAN - Tags: POLITICS MILITARY CONFLICT) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
ምስል Reuters

በሱዳን ምዕራባዊ ግዛት 9 አመት ሙሉ ውጊያ ሲካሄድ ቆይቷል ። የዳርፉር ግጭት የዓለምን ትኩረት የሳበው ግን ዘግይቶ ነው ። በተለይም የሱዳንን መንግሥት የሚደግፉት ታጣቂ የጃንጃዊድ ሚሊሽያዎች በግመሎች ላይ ሆነው በግዛቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎችንና ሰለማዊ ሰዎችን ሲያጠቁና ሲያድኑ የሚያሳይ ምስል ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ከሆነ በኋላ ነበር የአለም ህዝብ ለዳርፉር ግጭት ትኩረት መስጠት የጀመረው ። በዳርፉር ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 300 ሺህ እንደሚገመት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እጎአ በ2007 ካሳወቀ በኋላ የፀጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት 20 ሺህ የድርጅቱ ሰላም አስከባሪዎች ዳርፉር ሰፈሩ ። ከዚያን ጊዜ አንስቶ በግዛቲቱ ሰላም አስከባሪ ኃይል ቢኖርም አሁንም ሁኔታው አለመሻሻሉን ነው አሜሪካን በሚገኘው የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ባልደረባ Anne ባርትሌት የሚያስረዱት ። ባርትሌት የዳርፉርን ሁኔታ ለአመታት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርድሮችም ተካፍለዋል ። በአሁኑ ሰዓት የአንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሃላፊ ናቸው ።

« በርግጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ እንደታሰበው በእውነት ለሰዎች ጥበቃ ማድረግ ተስኖታል ። በኔ አስተያየት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃይሉን ማጠናከር አለበት ፤ ተጠያቂነቱንም ከፍ ማድረግ ይገባዋል ። እዚያ የሚገኙትን ሰላማዊ ሰዎች ለመርዳት ምን እየተደረገ እንደሆነም መከታተል ይኖርበታል ። በርግጥ ብዙዎቹ የእርዳታ ድርጅቶች ከዳርፉር ወጥተዋል ። በጣም ጥቂት ብቻ ናቸው ዳርፉር ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ። ሁኔታው እጅግ በጣም ተባብሷል ። »

Anne Bartlett bei der Sudankonferenz in Bonn 2012
አን ባርትሌትምስል DW

በዳርፉር ሁኔታው በጣም ውስብስብ ነው ። በመጀመሪያ የሱዳን መንግሥትንና በገንዘብ የሚደግፋቸውን ሚሊሽያዎች ይወጉ የነበሩት አማፅያን በዳርፉር ጉዳይ ከመንግሥት ከፍ ያለ የመወሰን መብት እንዲሰጣቸው ነበር የሚጠይቁት ። አሁን በዳርፉር የተለያዩ ግንባሮች አሉ ። የአማፅያን ቡድኖች በተደጋጋሚ ከመንግሥት ጋር ይዋጋሉ ። የተለያዩት የጎሳ አማፅያንም የመሪት ይዞታቸውን ለማስፋፋትና የፖለቲካ ተፅዕኖ ለማሳደር እርስ በርሳቸውም ይዋጋሉ ። ገበሬዎችና አርብቶ አደሮችም በተፈጥሮ ሃብቶች ይጋጫሉ ። ወሮ በሎችም በዳርፉር ይንቀሳቀሳሉ ። የሱዳን መንግሥት ለአማፅያኑ ምንም አይነት ሥልጣን መስጠት ስለማይፈልግ በግዛቲቱ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ወደ ኋላ ይጎትታል ሲሉ ታዛቢዎች ይወቅሳሉ ። ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳና ፍርድ ቤት በዳርፉር ተፈፅመዋል ባላቸው የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሽር ላይ የእስር ማዘዣ ቆርጧል ። ይሁንና የሱዳን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራህማት አላህ ሞሀመድ ክሱን ከፖለቲካ ጥቅም ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ያጣጥሉታል ። በዳርፉር የሰብዓዊ መብት ይዞታ ተበላሽቷል የተባለውንም አስተባብለዋል ።

« ለዚህ ምንም ማረጋገጫ የለም እኔ ራሴ ከ 2 ሳምንት በፊት ዳርፉር ነበርኩ ። እዚያ ያሉትን ከውጭ የመጡትን ከሞላ ጎደል አነጋግሬያለሁ ። አንዳቸውም በዳርፉር ስለ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ያነሱልኝ ነገር የለም ። ምናልባት ከሌሎች አገራት ወይም በሱዳን ከሌሎች አካባቢዎች ጋር አምታተውት ይሆናል ። »

ARCHIV - Ein Handout der African Union-United Nations Hybrid Operation in Darfur (UNAMID) zeigt einen bewaffneten Sudanesen am 19.05.2011 nahe Kuma Garadayat, einem Dorf in North Darfur im Sudan. Vieles deutet auf ein unruhiges Jahr auf dem schwarzen Kontinent hin. Schließlich sollen auch in etwa 30 Wahlen über neue Parlamente und Präsidenten entschieden werden. Allerdings ist der Konflikt in Darfur von einer Befriedung weit entfernt. Foto: Albert Gonzales Farran/epa/Handout Editorial Use Only No Sales (Zu dpa-Korr.: «Afrika vor Umbrüchen» vom 20.12.2011) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture alliance / dpa

የተባበሩት መንግሥታት በሱዳን ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ቢጥልም አሁንም ሱዳን ወደ ዳርፉር የጦር መሣሪያ ትልካለች መባሉን ሚኒስትሩ ሃሰት ነው ያሉት ። ስለዚሁ የተጠየቁት በዳርፉር የተባበሩት መንግሥታት ልዩ ልዑክና ዳርፉር የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ ኢብራሂም ጋምባሪ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ መጠይቅ መንግሥትና አማፅያን እስከተዋጉ ድረስ የጦር መሣሪያ መጠቀማቸው የማይቀር ነው ሲሉ ነበር ዲፖሎማሲዊ መልስ የሰጡት ። ጋምባሪ እንደሚሉት በዳርፉር ሁኔታዎች አሁን ከቀድሞው የተሻለ ደረጃ ላይ ናቸው ።

« እውነታው አሁን በብዙ የዳርፉር አካባቢዎች ሁኔታዎች በአጠቃላይ መሻሻል ይታይባቸዋል ። ይህም በእንግሊዘኛው ምህፃር UNAMID የሚባለው ሰላም አስከባሪ ኃይል የሠራዊቱን ሥምሪት እንዲያስተካክል ያስችለዋል ። የወታደሮቻችንን ቁጥር ማስተካከል መቀነስም ያስችለናል ።»

በአሁኑ ጊዜ 26 ሺህ የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል ዳርፉር ይገኛል ። ዳርፉር ከዚህ ያነሰም ይሁን ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ያስፈልግ አያስፈልጋት በመጪዎቹ ወራት የሚታወቅ ነው የሚሆነው ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ