1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳይምለር-ክራይስለር አውቶሞቢል አሠሪዎችና ሠራተኞች ስምምነት፧

ዓርብ፣ ሐምሌ 16 1996

እሽቱትጋርት፧ ጀርመን፧ የሚገኘው ታዋቂው የአውቶሞቢል ፋብሪካ፧ ዳይምለር-ክራይስለር አሠሪዎችና ሠራተኞች፧ ሌሊቱን ሙሉ ከተደራደሩ በኋላ፧ በ ፮ ነጥቦች፧ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ፧ Jürgen Schrempp ውሉ፧ ፍጹም እንዳረካቸው በመግለጽ፧ ለመላዋ ጀርመን አብነት ያለው ነው፧ እስከማለት ነው የደረሱት።

https://p.dw.com/p/E0fS
ምስል AP

O-ton(”Ich möchte hier ganz klar sagen..........Flexibilität.”
ጀርመን፧ የሥራ ሰዓትን መጠን በተመለከተ፧ አንድ-ወጥ ወይም አጠቃላይ ደንብ እንደማያስፈልጋት፧ በግልጽ ለመናገር እፈልጋለሁ። በጀርመን የሚገኙ ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች፧ ተግባራቸውን በሥርዓት ለማካሄድ፧ እንደገና ፋታ የሚያገኙበት ሁኔታ ያሻቸዋል፧ በሌላ አገላለጽ፧ ለአሠራራቸው የተፍታታ ይዞታ ሊኖር ይገባል« ብለዋል።
የጠቅላላ ሠራተኞች ኮሚቴ ሊቀ-መንበር፧ Erich Klemm የሥራ ቦታን አስተማማኝ ማድረጊያ ውል ስላሉት ስምምነት ሲናገሩ፧ የሚደበቅ ሁኔታ አይኖርም፧ ቁጠባውም ሆነ ቅነሣው፧ ያስቆጫል። ይህን ሐቅ መቀበል ያስፈልጋል። ሠራተኞች፧ እ ጎ አ ከ 2006 ዓ ም አንስቶ፧ ከደመወዛቸው 2.8 % ይቀነስባቸዋል። እርግጥ፧ አንድ ጊዜ ብቻ በሚሰጥ ማካካሻ ክፍያ ለማስተካከል ይሞከራል። እንዱስትሪ ኩባንያው የሆነው ሆኖ፧ በደመወዝ ቅነሣ፧ በዓመት ፪፻ ሚልዮን ያህል ዩውሮ ስለሚያተርፍ እርካታ ነው የተሰማው። ክሌም ቀጠል በማድረግ ከአሠሪዎች ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት፧ የሠራተኞች የሥራ ቦታ፧ እ ጎ አ እስከ 2012 ዓ ም አስተማማኝ ሆኖ የሚዘልቅበት ውል የታሠረ መሆኑን አስረድተዋል።
Sindelfingen በተሰኘው ቦታ እ ጎ አ በ 2006 ዓ ም የሜርሴደስ ሲ እና ኢ «ሞዴል« ምርት እንዲቀጥል ይደረጋል። በ Untrtürkheim እና ማንሃይም የአውቶሞቢሎቹ ሞተርና የሞተር ክፍል ይመረታል። የ ፮ሺ ሰዎች የሥራ ቦታም ለረጅም ጊዜ አስተማማኝ ሆኖ እንዲቀጥል ይደረጋል። የሜርሴድስ ዋና ሥራ አስኪያጅ፧ Jürgen Hubbert፧ የዕረፍት ጊዜንና የፈረቃ ሥራን አስመልክተው ሲናገሩ፧ የባደን ቩርተምበርግ ኑዋሪዎች፧ ከሰሜን ጀርመናውያን በዓመት ፸፪ ሰዓት ያነሰ ይሠራሉ በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
O-ton(Von den ja sehr.......
«በ Sindelfingen እና በብሬመን መካከል የ፸፪ ሰዓቱ የሥራ ሰዓት ልዩነት ቢጣጣም እንኳ የ፵፪ ሰዓት ልዩነት መኖሩን ማጤን ይገባል። ይሁንና ፫ በዓላት መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም፧ ከእኛ ቁጥጥር ውጭ በሆኑት፧ በእነዚህ በዓላት በአጠቃላይ ፳፬ የሥራ ሰዓቶች ባክነው ይቀራሉ። የሆነው ሆኖ፧ በአወንታዊ የሥራ እንቅሥቃሴ መንፈስ ተግባራችን ማከናወኑን እንቀጥላለን« ብለዋል።።
የ Steinkühler የ ፭ ደቂቃ ዕረፍት የሚባለው ወደፊት እንዲሠላ ይደረጋል። ሰፋ ያለ ወጪ የሚያስወጣው፧ የማታ የፈረቃ ሥራ ይሠረዛል። በሰዓት የ ፴፱ ሰዓቱ ሥራ፧ ሠራተኞቹ በዕድሜ እይገፉ ሲሄዱ፧ የሥራ ጊዜያቸው በሳምንት ወደ ፴፬ ሰዓት ተኩል ዝቅ እንዲልላቸው ይደረጋል።
ኢንዱስትሪ ኩባንያው፧ የሚያንሠራራበት ፋታ እንዲያገኝ፧ ሠራተኞች የሥራ ዋስትና ተሰጥቶአቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ፧ ቁጠባም እንዲደረግ ከተደረሰበት ስምምነት ጋር ተያይዞ፧ የኢንዱስትሪው ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት፧ ከደመወዛቸው ፲ ከመቶ እንደሚቀነስባቸው ነው የተገለጠው።