1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድራማ ቀረፃ በአዲስ አበባ

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2005

በማዳመጥ መማር የተሰኘው በዶቼ ቬለ እና በጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የሚቀርበው አዝናኝ እና ትምህርታዊ ተከታታይ ድራማ 6ኛ ዙር ቀረፃ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/19ABv
Titel: LBE Produktion 2013 Äthiopien Schlagwörter: Schauspieler, Äthiopien, LBE Datum: 18.07.2013 Bildrechte : M.Sileshi (DW)
ምስል DW/M.Sileshi
Titel: LBE Produktion 2013 Äthiopien Schlagwörter: Schauspieler, Äthiopien, LBE Datum: 18.07.2013 Bildrechte : M.Sileshi (DW)
ምስል DW/M.Sileshi

ዘውትር ዓርብ ከወጣቶች ዓለም ዝግጅት በኋላ ይቀርባል። LEARNING BY EAR ወይንም በማድመድ መማር የተሰኘው ተከታታይ የራዲዮ ድራማ። ከድርሰት ፁሁፍ፣ ትርጉም እና ዕርማት በኋላ ለድራማ ቀረፃ የዶይቸ ቬለ ባልደረቦች ወደ ስድስት የአፍሪቃ ሀገራት ይጓዛሉ። ለአማርኛው ቀረፃ ማንተጋፍቶት ስለሺ እና ጌርድ ጊዎርጊ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ይገኛሉ። እነሱ እንደገለፁልንም ቀረፃው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እና እየተጠናቀቀ ነው።

ይህ «መንታ መንገድ ላይ ያለ ትውልድ ከባድ አማራጮችን መጋፈጥ» በሚል ርዕስ የሚቀርበው የራዲዮ ድራማ ርዕሱም እንደሚለው ወጣቶች የተለያዩ አማራጮች እና ፈተናዎች ሲገጥሟቸው ያወሳናል። አዲሱ ተከታታይ ድራማ እስኪጀምር በሙስና በስደት እና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ባለ 10 ክፍል ድራማዎች ይጠብቋችኋል። ከአማርኛ ውጪ በሃውሳ፣ ኪስዋሂሊ፣ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛና ፓርቱጋልኛ ቋንቋዎች የበማድመጥ መማር ድራማ ተቀርፆ ይተላለፋል።

የዘንድሮ የበማድመጥ መማር ዝግጅት የድራማ ቀረፃን በተመለከተ ማንተጋፍቶትን አነግረንዋል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ