1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድርቅ ተፅዕኖ በኤኮኖሚ ላይ

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ መጋቢት 21 2008

በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ የአስቸኳይ ርዳታ ፈላጊው ቁጥር 10,2 ሚልዮን ደርሶዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት እና ግብረ ሠናይ ድርጅቶች ድርቁ ያስከተለው የምግብ እጥረት እየከፋ እንዳይሄድ ጥረታቸውን አጠናክረው በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/1IMBf
Äthiopien Hunger Hungerhilfe
ምስል Reuters/T.Negeri

[No title]

የአየር ንብረት ለዉጥን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ድርቅ ተከስቶዋል። በአገሪቱ የግብርና ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮዋል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ በዚህ የበጀት ዓመት 11 ከመቶ የኤኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ያስቀመጠችውን እቅድ እንደማታሳካ እና እድገቱ በሰባት እና በ10 ከመቶ መሃል እንደሚሆን የምጣኔ ሀብት ጠበብት ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱ ባለ ሁለት አሀዝ የኤኮኖሚ እድገት ቢቀዛቀዝም እድገቱ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቁት።

ከ2007 ዓ/ም አጋማሽ ጀምሮ ድርቅ በሰዎች እና በቀንድ ከብቶች ላይ ከፍተኛ ችግር አድርሶዋል። ሌሎች የግብርና ምርቶች ላይም ከፍተኛ ችግር ማድረሱ ይታወሳል። እንደ የደቡብ ብሄር ብሄሬሴቦች እና ህዝቦች፣ እንዲሁም፣ የኦሮሚያ ክልልን በመሳሰሉ በበልግ አምራች አካባቢዎች ድርቁ በዓመታዊ የግብርና ምርት ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳርፍ መንግስት ክትትል እያደረገ መሆኑን በግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ምንስቴር የህዝብ ግኑኝነት አለፊ አቶ አለማየሁ ብርሃኑ ለዶይቸ ቬሌ ተናግረዋል።


ከኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርት መጠን የግብርናው ዘርፍ ባለፈው ዓመት 40 ከመቶ ድርሻ እንደነበረው የኢትዮጲያ ፋይናንስ ሚንስቴር ያወጣው መረጃ ያመለክታል። ድርቁ በባለፈዉ የመኸር ወቅት በግብርና ምርቶች ላይ ያሳረፈውን ጫና ለማወቅም የግብርና ሚንስቴር ከማእከላዊ ስታትትሲክስ ኤጄንስ ጋር እየሰራ መሆኑን አቶ አለማየሁ ገልጸዋል። የግብርና ሚንስቴር ይህን ችግር ለመቋቋም እና ግብርናዉ የኤኮኖሚዉ መሰረት ሆኖ እንዲቀጥል ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን አቶ አለማየሁ ይናገራሉ።


እሄን ጉዳይ በተመለከተ በዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ድረ ገፅ ላይ ዉይይት አካሄዴን ነበር። አበዛኞች አስተያየት ሰጭዎች መንግስት በዝናብ ላይ የተመሰረተዉን የግብርና ፖሊስ መከለስ እንዳለበት ጠቁመዋል። ሌሎች ደግሞ በበኩላቸዉ ችግሩ ያለዉ አገርቱ የምትከተለዉ የፖሊቲካ ኤኮኖሚ ስርዓት መሆኑን ገልጸው የኤኮኖሚው እድገት ከቁጥር ባለፈ ገሀዱን እንደማያንጸባርቅ አስተያየታቸዉን አጋርተዋል።

Safia works in her fields, Ethiopia
ምስል CC / Oxfam International

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ