1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶይቼ ቬለዋ ንጋት ከተማ

ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2007

በጣም ሆዴን አባብቶታል ከአድማጮቼ መለያየቴ» ። አድማጮቼ ችግራቸው ችግሬ ሆኖ ይሰማኛል ። የሚልኩት ደብዳቤ ማለት መልክት ሁሉ ፍቅር ያሳድርብኛል ።»

https://p.dw.com/p/1EnPo
DW Amharische Redaktion Negat Ketma und Hirut Melesse im Studio Abschied
ምስል DW/H. Melesse

« ላላፉት 10 ዓመታት የአድማጮች ማሕደርን ያዘጋጀችው ንጋት ከተማ። የዶይቼ ቬለዋ ንጋት ከተማ በርካታ አድማጮች አልዋት ብዙዎች እስታንፋሳችን ብርኃናችን ሲሉም ከልብ ያወድሷታል። የአድማጮች ማሕደር አዘጋጅ ንጋት ከተማን። ከ 28 ዓመት የአገልግሎት ዘመን በኋላ ከጥቂት ቀናት በፊት ከዶይቼ ቬለ በጡረታ የተሰናበተችዉ ንጋት ከተማ የአድማጮች ማኅደር እንግዳችን አድርገን ይዘናታል። በመግቢያዉ ላይ ከዝግጅቱ መለየትዋን ያሳደረባትን ስሜት ነበር የገለፀችልን። በዚህ ዝግጅት ወ/ሮ ንጋት ከተማ በዶይቼ ቬለ አገልግሎትዋ በተለይም ባለፉት 12 ዓመታት ያለማቋረጥ ያዘጋጀችዉን የአድማጮች ማኅደር ዝግጅት ትዝታዎችዋን ታካፍለናለች መሉ ቅንብሩን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ