1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በሕንድ

ሐሙስ፣ ኅዳር 11 2001

ምጣኔ ሐብቷ በሚያረካ ሥሌት እየተንቻረረ- ቴክኖሎጂዋ በሚያስደንቅ ፍጥነት እየረቀቀ ነዉ።በቅርቡ የምርምር መንኮራኩር ወደ ጨረቃ ልካለች።የኒኩሌር ቦምብ ባለቤትም ነች።የዚያኑ ያክል የድሆችም ሐገር ናት።ሕንድ

https://p.dw.com/p/Fyly
የሕንድ መንኮራኩርምስል AP

የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ቫልተር ሽታይን-ማየር ሕንድን ለሰወስት ቀናት ለመጎብኘት ትናንት ወደ ኒዊ ደልሒ ሔደዋል።ሽታይን ማየር የመሯቸዉ የጀርመን መልዕክተኞች በከሕንድ ቆታቸዉ ከሐገሪቱ ባለሥልጣናት፥ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ከኩባንያ ባለቤቶች ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ሕንድ በአለም አቀፍ መድረኮች ሥለምታበረክተዉ አስተዋፅኦ ትኩረት ሰጥተዉ ይመክራሉ።የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስር የሚያደርጉት ጉብኝት ከፍተኛ የምጣኔ ሐብት እድገት በማሳየት ላይ ያለችዉን የሕንድንና የጀርመንን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ይረዳል።ዲርክ ሙለር የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናክሮታል።