1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመናዉያን የገና በአል ባህላዊዉ መሰናዶ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 18 2002

በጀርመን በአመቱ እጅግ የሚወዱትን የገና በአላቸዉን ለሁለት ቀናት በተከታታይ አክብረዋል። ያለፈዉ ሃሙስ ምሽትን እየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት ቅዱሱ ምሽት በማለት ሲጠሩት በነጋታዉ ቀዳማዊ ገና ሲሉ ቀኑን ይሰይሙታል

https://p.dw.com/p/LE9D
የተጠበሰዉ የዳክዩ ስጋምስል picture-alliance/ dpa
በመቀጠል ያለዉን ቀን ደግሞ ዳግማዊ ገና በማለት ገናን ሁለት ቀን አክብረዉት ይዉላሉ። ከምዕራቡ አለም ጀርመናዉያን በገና በአል አከባበራቸዉ ለየት ያሉም እንደሆን ይታወቃል። የገና በአል ከመድረሱ አራት ሳምንት ጀምሮ የሚደረገዉ ባህላዊ ዝግጅት መሰናዶ ህጻን አዋቂዉን ምነዉ ገና በደረሰ እንዲል ሲያደርገዉም ይታያል። በዛሪዉ ዝግጅታችን ጀርመናዉያን በገና በአል የሚያደርጉት ባህላዊ መሰናዶ ስር ያቆየናል ለጥንቅሩ አዜብ ታደሰ ነኝ መልካም ቆይታ
ትናንት ከትናንት በስታያ ከዝያም አልፍ ከሃሙስ ምሽት ጀምሮ ሶከበር የቆየዉ የፈረንጆቹ ገና እንደ ደንቡ ቢጠናቀቅም በአሉን ማክበር ዛሪም የቀጠሉ አልጠፉም፣ ለምን ዛሪ ሰንበት ነዉ። ከበአል የተረፈም የተዘጋጀ ጣፋጭ ምግብ አይጠፋም እና በቤተሰብ በአልነቱ የሚታወቀዉና በጀርመናዉያን ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነዉ የገና በአል ጀርመናዉያን አመት በገባ በመጨረሻዉ ወር ከገባ ጀምሮ የበአሉን መድረስ ይጠባበቃሉ። በየአደባባዩ ተንቀሳቃሽ በሆነ የእንጨት ጎጆ ቤት ዉስጥ የተለያየ ነገር በመሸጥ ቤቱንም ሆነ መደብሮችን በማሸበራረቅ ይጠብቁታል። ሌላዉ በገና በአል ህዝቡ ለወዳጅ ዘመዱ በዚሁ ገና በአል የሚሰጠዉን ስጦታ ለመግዛት ወደ መድብር የሚሄደዉም ህዝብ ይበዛል። በያዝነዉ አመት ታላላቅ መደብሮች ገዥዎችን ለመሳብ ለገና በአል ትልቅ ቅናሽ ማድረጋቸዉን ገና ህዳር ወር አጋማሽ ላይ ነዉ ማስታወቅያቸዉን ማዉጣት የጀመሩት። የቤተሰብ በአል እንደመሆኑ መጠን ልጆች ከወላጆቻቸዉ ጋር የሚገናኙበት ቀን በመሆኑም የበአሉ እለት የሚበሉትን ገና ከወር በፊት ነዉ አስቀድመዉ መነጋገር እና ይህን አዘጋጅተን ብንበላ ብለዉ የሚስማሙት። ታድያ በበርካታ ጀርመናዉያን ዘንድ በተለይ በዚህ በገና በአል የዳክዩ ስጋ መብላት የተለመደ ነዉ።
ሰአቱ ምን ግዜ ሮጠ በሚባልበት በዚህ ወቅት ጀርመናዉያን ከስራ ቤት ከቤት ደሞ ወደ ሌላ ጉዳያቸዉ ሲሯሯጡ፣ እንደ ገና በገና በአል ወቅት አስፈላጊ የተባለዉን ስጦታ ለመግዛት ስለማያመቻቸዉ፣ በበአሉ ምሽት የሚበሉትን ምግብ ከሆቴል ቤት እቤታቸዉ ድረስ እንዲመጣላቸዉ አዘዉ የሚበሉም በርካቶች ናቸዉ። እርቁ ሳንሄድ፣ እዚህ የሰላሳ ሁለት ቋንቋ ስርጭት ክፍል፣ ያቀፈዉ ዶቸ-ቬለ፣ አብዣኞች ይህን የአዉሮጻዉያኑን የገና በአል አክባሪዎች ስለሆኑ፣ ታዋቂዉ የዶቸ ቬለ ምግብ ቤት የበአሉ ቀን ስራ ያላቸዉ እንደገና እምድጃ ላይ ግዜያቸዉን እንዳያባክኑ ለገና በአል የሚሆን ምግብ በመስራት እርዳታ እንደሚያቀርብ በመስሪያ ቤቱ የዉስጥ የመገናኛ መረብ ማስታዉቂያዉን፣ በአሉ ሁለት ሳምንት ሲቀረዉ ነበር ያወጣዉ። በነገራችን ላይ የዶቸ ቬለ የምግብ ቤት ጣእም ያለዉ ምግብ መስራቱ ይነገርለታል። ታድያ ለገና በአልም ትልቁ የዳክዩ ጥብስ መቶ ሰባ ብር፣ አነስ ያለዉ መቶ ሃያ ብር፣ እንዲሁም አነስተኛዉ ዘጠና ብር ተሸጦአል። ለዳክዩዉ ማባያ የድንች ቅቅል እንዲሁም ቀላ ያለ የጥቅል ጎመን ሰላጣ ጋር በስራ የተጠመዱ ጋዤጠኞች ከስራ መልስ ከሳምንታት በፊት ያዘዙትን ለገና በአል ምሽት የሚበላዉን ምግብ በየተራ ሲወስዱ ታይተዋል። ለነገሩ የዶቼ ቤለ ጋዤጠኞች ብቻ ሳይሆይሆኑ ይህንን እድል በየተጠቀሙት ምድጃ ገብቶ ከመርመጥመጥ ጠቦጥ በግ የሚያክለዉን ዳክዩም ሆነ ሌላ የዶሮ ዝርያ ባለሞያ አጋም አስመስሎ በቅመም አሳብዶ ጠብሶ ከጎኑ ድንች እና የጥቅል ጎመን ጥብስ እና ሰላጣ ገንዘብ ከፍል አድርጎ መዉሰዱ የሚቀላቸዉ ጀርመኖች ጥቂት አልነበሩም። ታድያ ያ አጋም መስሎ የተጠበሰዉ የበግ ጠቦት የሚያክለዉ ዶሮ በትኩሱ ካልተበላ እና ካደረ ጅማት ሆኖ አልታከኝ ስለሚል ሁሉም መበላት አለበት በነጋታዉም ደጋሹ ወደሌላዉ ቤት ሄዶ እዝያ የተደገሰዉን ነገር ይበላል። ምሽት ላይም ኬክ ቡና ይጠጣል ይበላል።
Kinder unterm Tannenbaum
ምስል DW

የልደት በአል ብዙ ገንዘብ በማስወጣት ተወዳዳሪ የለዉም፣ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ በማለት ሁሉም ለልጆቻቸዉ ለዘመድ ወዳጆቻቸዉ በዚህ በአል ለስጦታ የሚሆን ነገር ይሸምታሉ፣ ሌላዉ ጀርመናዉያን በገና በአል ትልቅ ቦታ ያለዉ የገና ዛፍ ነዉ። ጥድ ዛፉ እስከ ሰላሳ አምስት ይሮ ያኣወጣል ትንሹ አስራ አምስት ይሮ፣ ጀርመናዉያን የጥዱ ሽታ ቤታቸዉን ሲያዉደዉ እዉነትም የገናን በአልን ማክበራቸዉን በእዉነት ይቀበሉታል። በቀለማት ያሸበረቀዉ የገና ዛፍ ስር ስጦታ በልዩ ወረቀትተጠቅልሎ በመኖርያ ቤት ዉስጥ ብቻ ሳይሆን በመደብሮች ዊስጥም መታየት የሚጀምረዉ ታህሳስ ወር አጋማሽ ጀምሮ ነዉ። የክረምቱ ብርድና በረዶ ሳይበግረዉ አረንጓዴ ሆኖ ክረምትን የሚወጣዉ የጥድ ዛፍ ለጌጥነት ተመርጦ በላዩ ላይ የሚደረገዉ መብራት እና ጌጣጌጥ ተጨምሮበት ክረምትን ለማስዋቢያ የገናን በአል ማሳያ ተደርጎ ለመጀመርያ ግዜ በዚሁ በጀርመን እንተ ጀመረ ይነገራል።
አዜብ ታደሰ