1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንና የአንጎላ የኤኮኖሚ ግንኙነት

ሐሙስ፣ ኅዳር 19 2000

ጀርመን በአንጎላ ነዳጅ ዘይት ላይ ዓይኗን አስፋለች

https://p.dw.com/p/E0cW

የጀርመኑ የምጣኔ-ሐብት ሚኒስትር ሚሻኤል ግሎትስ በፊታችን ሰኞ ሰፊ የልዑካን ቡድን አስከትለው ወደ አንጎላ ያመራሉ። አንጎላ ነዳጅ ዘይት አምራች መሆኗ ሲታወቅ ትብብሩንም በተለይ በዚሁ በኤነርጂው ዘርፍ ለማጠናከር ነው የሚታሰበው።

በዓለም የኤነርጂ ገበያ ላይ የአንጎላ ሚና እየጠነከረ በመሄድ ላይ ሲሆን አገሪቱ ውስጥ ገንዘባቸውን ለማዋል የሚፈልጉት የውጭ ባለሃብቶችም ብዙዎች ናቸው። የጀርመን መንግሥትም ለኢንቨስትመርት ዋስትና በመስጠትና ብድር በማቅረብ ትብብሩን ለማስፋት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጀርመን ልዑካንና በአንጎላ መንግሥት መካከል የፊናንስ ውል መፈረሙ አንዱ የጉብኝቱ ዓላማ ነው። በውሉ መሠረት አንጎላ ወደፊት ለጀርመን ሰፊ የነዳጅ ዘይት አቅርቦት ማድረግ ትችላለች።