1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንና የአፍሪቃ ትብብር፣

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 21 2001

ጀርመን የአፍሪቃ ሐገራትን ግጭትና ጦርነቶች ለማስወገድ በሚደረገዉ ጥረት በንቃት እንደምትሳተፍ የሐገሪቱ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ደ-ኤታ አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/Hgbz
የአፍሪቃ ኅብረት ስብሰባ፤ምስል picture-alliance/ dpa

ሚንስትር ደኤታ ፔተር አሞን ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት አምባሳደሮች እንደተናገሩት መንግሥታቸዉ በአፍሪቃ ሠላም ለማስፈን በሚደረገዉ ሁለንታዊ ጥረትን ለመደገፍ ተጨባጭ’ እርምጃዎችን እየወሰደ ነዉ።ሚንስትር ደ-ኤታዉ አዲስ አበባ የገቡት በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የሚሰሩ ሠላሳ አምስት የጀርመን አምባሳደሮችን አስከትለዉ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ ፔተር አሞን ጀርመን ለአፍሪቃ ሕብረት የሠላምና የፀጥታ ምክር ቤት በሃያ-ሚሊዮን ዮሮ የምታሰራዉን ሕንፃ ቅርፅ ዛሬ መርቀዉ ከፍተዋልም።--ታደሰ እንግዳው፣

ነጋሽ መሐመድ፣

ተክሌ የኋላ፣