1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመንየውጭ መርህ ና ፕሬዝዳንት ጋውክ

ማክሰኞ፣ የካቲት 18 2006

አዲሱ የጀርመን ትልቅ ጥምር መንግሥት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የጀርመን የውጭ የፖለቲካ መርህ መጠናከር ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ። ይህም ተግባራዊ እንዲሆን የተወሰኑ የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በማሳሰብ ላይ ናቸው ።

https://p.dw.com/p/1BFGR
Gauck DW Interview 21.02.2014
ምስል Bundespresseamt/Jesco Denzel

ጀርመን በዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ውስጥ በንቃት እንድትሳተፍ ከሚያሳስቡት መካከል አንዱ የጀርመን ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ ናቸው ። ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ጀርመን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚጠበቅባትን ድርሻ መውጣት እንደሚገባት አስገንዘበዋል ።

ከአውሮፓ በህዝብ ብዛትና በኤኮኖሚ ጥንካሬ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ጀርመንበዓለም ዓቀፍ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ውስጥ ያላት ሚና አነስተኛ መሆን ማነጋገሩን እንደቀጠለ ነው። ከ2 ተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የጀርመን የውጭ የፖለቲካ መርህ ይበልጡን ወደ አጋሮቿ አሜሪካን ፈረንሳይና ብሪታኒያ ያደላ ሆኖ በሌላው የዓለም ክፍል በሚካሄዱ ወታደራዊ ተልዕኮዎች እንዳትሳተፍ የሚገድብ ነበር።ይህ የሆነውም ባለፈው ታሪኳ ምክንያት የሃገሪቱ ህገመንግሥት በወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እንዳትሳተፍ በመገደቡ ነበር። የጀርመንፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ ባለፈው ሳምንት አርብ ለዶቼቬለ በሰጡትቃለምልል ስምክንያቱን አብራርተዋል።

« የዚህችን ሃገር ይዞታ በብዙ መልኩ ስናየው በዴሞክራሲም ያላትን ታዓማኒነት ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራትና ዓለም ዙሪያ ካሉ ሌሎችም ጋር ስናነፃፅረው ምንም ዓይነት ጉድለት አላገኘሁበትም ። ስለሆነም በዚህ ደረጃ ከሚገኙ ሃገሮች ጋር ሲነፃፀር እኛ በሰፊው ቁጥብነት የማሳየታችንንም ሆነ ችላ የማለታችንን በቂ ምክንያት ልገነዘበው አልችልም ። በውጭ ሃገራት የኛ ተሳትፎ በአዎንታዊ መልኩ ነው የሚታይ በሃገር ውስጥም ቢሆን ርግጥ ነው ግንዛቤ የማግኘት ገደብ ምናልባትም እዚህ ላይ ባህላዊ ገደብ የሃሳብ ግጭት ሲያስከትል እናያለን ።በብዙ ጀርመናውያን መካከል እኛ ይህን ለማድረግ ብቁ አይደለንም የሚል ስሜት አለ ። ለምን ቢባል ፅልመት የለበሰ ያለፈ ታሪክ ስላለን ነው ይህንንም አመለካከት ብዙ የጀርመን ህዝብ የሚጋራው ነው ። »

Deutsche Außenpolitik Merkel Steinmeier im Flugzeug 18.12.2013
ምስል Reuters

ሆኖምእጎአከ1998 እስከ2005 ጀርመንንበመሩትበመራሄመንግሥትጌርሃርድሽሮደርዘመነመንግሥትእጎአበ1999 ለመጀመሪያ ጊዜ ጀርመን በሰርቢያው ጦርነት ተሳትፋለች። ከዚያን ጊዜ አንስቶም ጀርመን ወታደሮቿንወደ ውጭ እያዘመተች ቢሆንምበሙሉ አቅሟ ተካፋይ አለመሆኗ ያስተቻታል። ሽሮደርን በተኩት በመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል አመራርም የጀርመን የውጭ ወታደራዊ ተሳትፎ ያን ያህል አጥጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚነገረው።የ ቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለም በሥልጣን ዘመናቸው ሃገሪቱ በዓለም ዓቀፍ ወታደራዊ ተልዕኮዎች መካፈሏን ሲከላከሉ ነው የቆዩት። ይህም ጀርመንን በዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ሃላፊነቷን ከመወጣት ወደ ኋላ በማለት ወይንም በአድፋጭነት እንድትታይ እንዳደረጋት የጀርመን ፕሬዝዳንት ዮአሂም ጋውክ ባለፈው ወር ሙኒክ ጀርመን ውስጥ በተካሄደው ዓለም ዓቀፍ የፀጥታ ጉባኤ ላይ ተናግረው ነበር። የጀርመን አጋሮች ዋሽንግተን ፓሪስ ናለንደን ጀርመን ዓለም የሚጠበቅባትን ድርሻ ባለመወጣቷ ቅር መሰኘታቸው አልቀረም ። ከ3 ዓመት በፊት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የሊቢያውን ጦርነትሲያፀድቅ ጀርመን አለመስማማቷ እነዚህኑ ወገኖች ማበሳጨቱ የቅርብጊዜትዝታ ነው። የጀርመንፕሬዝዳንት ዮአሂምጋውክየጀርመንየፖለቲካ መርህ የማውጣት ወይም የመቅረፅ ሥልጣን ባይኖራቸውም ጀርመን በዚህ በኩል እንቅስቃሴዋ ይበልጥ እንዲጠናከ ርመጠየቃቸውን ቀጥለዋል ። ጋውክ ይህን ሲሉ የሚጠናከረው ዲፕሎማሲያዊው ተግባርወይ ስሌላውም ተጨማሪ ጉዳይ አለ ተብለው ከዶቼቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ በቅርቡከጎበኟትከህንድጋርሊደረግየሚገባውንግንኙነትበምሳሌነትበማንሳትነበርየመለሱት።

« ርግጥነው ከሁሉ አስቀድሞ በመጀመሪያ ሁሉም ነገር ከዲፕሎማሲ ጋር የተገናኘነው። በዲፕሎማሲው ስር የልማት ትብብር ሥራዎችም ይካተታሉ። ለምሳሌ በቅርቡበጎበኘኋት በህንድ የጀርመን የልማትትብብር ምን መሆን እንዳለበት፣ በሚሊዮኖችየሚቆጠር ገንዘብ የትእደገባ ፣ማሰብ አለብን። ለአካባቢ ጥበቃ ለአዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ለመጪው ዘመን ቴክኖሎጂ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ማስቀመጥም አስፈላጊ ነው። በዚህ ተግባርም ፣ከኛ ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች እንደ አካባቢጥበቃ በመሳሰሉ ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮችውስ ጥፍላጎትእንዳለን እናሳያለን።»

ጋውክ ከዚህን መሰሉ የልማት ትብብር በተጨማሪ በውጭው ዓለም ድህነትንና ማህበራዊ ውዝግቦች በማስወገድ ረገድም ጀርመንየበኩሏን ሚና ልትጫወት እንደሚገባትምተናግረዋል።

« በሌላበኩል ብርቱ ድህነት የተንሰራፋባቸውን ቦታዎች ስንመለከት ይህም በፊናው ማህበራዊ ውዝግቦችን ይቀሰቅሳል። እየተባባሰም ስለሚሄድ ብዙውን ጊዜ የብሄረሰቦችን ግጭት ወይም የሃይማኖትም ልዩነት መሠረት ያደረገ ማህበራዊ ውዝግብን ያቀጣጥላል። ይሄምሲሆን ውዝግቡ የርስ በርስ ጦርነት በሚመስል ሁኔታ ሊካሄድ ይችላል።እናም ይህ ከመሆኑ በፊትውዝግቡን ለመግታት መሰማራት ይጠበቅብናል። የልማት ተራድኦ ተግባራችንን የምናከናው ነው ሰዎች የተሻለ ማህበራዊ ኑሮ እንዲኖራቸው ለማገዝ ነው።በሌሎቹ የዓለም ክፍሎችም የውዝግብ መነሻዎችንበጥልቀት መመልከት ይገባናል፤ርግጥ ነው በመጀመሪያ ደጃፋችንካለው መጀመር ይኖርብናል።

Bundeswehr Ausbildungsmission in Somalia
ምስል picture-alliance/dpa

ጀርመን በዓለም ዓቀፍ መድረክ ይበልጥ ተሳታፊ እንድትሆን የሚጥሩት ጋውክ ብቻ አይደሉም።በአዲሱ ጥም ርመንግሥት የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እና የመከላከያ ሚኒስት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየን እንዲሁም ሌሎችም ባለስልጣናት የጀርመን ዓለም ዓቀፍ ተሳትፎ ውስን መሆን የለበትም የሚለውን አቋማቸውን ደጋግመው በማሰማት ላይ ናቸው ።የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልም በጀርመን ጦር ወታደራዊ ተሳትፎ ረገድ ለዓመታት ይከተሉት የነበረውን ግትር መርሃቸውን እንዳላሉ የሚያመልክቱ እርምጃዎችን ወስደዋል።ሜርክል፣የጀርመን ጦርየማሊወታደራዊተልዕኮእንደሚጠናከርና በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ለሚገኘው ለፈረንሳይ ጦር ድጋፍ እንደሚሰጥ ማሳወቃቸው ይህንኑ የሚያመለክት ነው ።ጀርመን በአውሮፓና በቀሪው የዓለምክፍል ሃላፊነቷን እንደምትወጣ ያሳወቁት ሜርክል ያን ካላደረገች ግን የወዳጆቿንና የራሷም ፖለቲካውና ኤኮኖሚ መጉዳቷ እይቀርም ሲሉም አስገንዝበዋል።ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሽታይንማየር ደግሞ የጀርመንን የውጭ የፖለቲካ መርህ ለማጠናከር ይበጃሉያሏቸውን እቅዶች ዘርዝረዋል።ከነዚህም አንዱ በዩሮ ቀውስ ምክንያት በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ሲከናወን የቆየውን ከአውሮፓ ህብረት ጋር የሚደረገውን ግንኙነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲመለስ ማድረግ ነው።ከዚህ ሌላ በተለይ ከፈረንሳይ ጋር ያለውን ትብብር ማሻሻልም ሌላው ዓላማቸው ነው።ይህን ለማሳካት ያሰቡትም ሽፒግል የተባለው የጀርመን መፅሄት ድረ ገፅ እንዳስነበበው ጀርመን የፈረንሳይንየአፍሪቃተልዕኮን ስትደግፍ ፈረንሳይ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት በምሥራቅ አውሮፓ ሃገራት የሚከተለውን መርህ ጀርመን እንድትመራ ድጋፍ ትሰጣለች።መከላከያ ሚኒስትር ፎንዴርላየን ደግሞ ከዚህ በላይ ለመሄድ ነውያሰቡት።ጀርመን ትልቅ ሚና የምትጫወትበትየ ጋራየአውሮፓየፀጥታመርህ እንዲዘጋጅ ነው ፍላጎታቸው ።ጋውክባለፉትዓመታትበተለያዩየዓለምክፍሎች የተከሰቱትን ግጭቶች ለማስቆም ፈጥኖ ባለመንቀሳቀስ የደረሰውን ጥፋት በማስታወስ ንግግርብቻበቂአይደለምበተግባርም ይተርጎምይላሉ ።

« በጦር መሣሪያ ኃይል አንዳንድ ተግባር መፈፀም ጥሩ አይደለም ። ሆኖም ደግሞ አንዳንዴ ከዚህ የከፋ የሚሆነው በጎ ማድረግ የሚችሉት መሣሪያዎቻቸውን ደብቀው መጥፎዎቹ በጦር መሣሪያቸው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ሲፈቅዱላቸው ነው ። ለዚህም በቂ ማስረጃና ምክንያቶች አሉ ። በአውሮፓ ውስጥ በስሬብሬኒቻ ቦስኒያ የሆነውን እናውቃለን ። ጥሩ ነገር ብቻ መናገሩ የሚረዳው ነገር የለም በሩዋንዳም አይተናል ። ጣልቃ ገብቶ ለግድያ የተሰማሩ ሰዎችን ለማስቆም በአፀፋው እርምጃ ባለመውሰዳችን ለደረሰው ነገር ምስክሮች ነን ። »

አንዳንዴ መፍትሄ ለመፈልግ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ትክክለኛውን እርምጃ መወሰዱ አዳጋች ሊሆን ይችላል ያሉት ጋውክ በአንዳንድ ሁኔታዎች ከመጥፎና ከእጅግ መጥፎ መካከል አንዱን መርጦ የመወሰን ሁኔታ ሊያጋጥም እንደሚችልም በቃለ ምልልሱ ተናግረዋል ። በአውሮፓ ምድር ከሰሞኑ ደም ያፋሰሰው የዩክሬኑ ውዝግብ ጋውክ በቃለ ምልልሱ ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ ነበር ።በየትኛው መልኩ የህዝብን ፍላጎት መጠበቅ እንደሚገባ ነው የተናገሩት ።

Deutschland Bundesmarine Schnellboot
ምስል imago/C. Thiel

« በዛ ያለው ምናልባትም አብዛኛው ህዝብ ፊቱን ወደ አውሮፓ ቢመልስ እንደሚጠቀም ነው የሚሰማው

። ይህም ሲሆን በአውሮፓ ትልቁ ኃይልና በአውሮፓ እጅግ ትልቁ ሃገር ወደ ኋላ ማፈግፈግ ሳይሆን ይሄ ፍላጎታቸው እንዲሟላ ማደፋፈርና በሰላማዊ መንገድ የሚስተካከልበት ሁኔታ በውጭው ድንበራችንም ቢሆን እሴቶችን መሠረት ባደረገ ስርዓት እንዲያድግ ምንጊዜም በአፅንኦት ማሳወቅ ይኖርብናል ። እዛ ያሉ ሰዎች ድሮ ጀምሮ በተለይ ከፊሉ ምዕራባዊው ዩክሬን መንግሥትም ጭምር ከአውሮፓ ጋር እንደተቆራኙ ነው የሚሰማቸው ። አሁንም ቢሆን የቆዩ ባህሎች ልማዶች እነዚህ ሰዎች ወደ ሞስኮ ፊታቸውን ከማዞር ይልቅ ወደ ምዕራብ ፊታቸውን የማዞር ዝንብሌ እንደነበራቸው ይታወቃል እርግጥ ሁሉም አንድ ዓይነት እንዳልነበረ የምናውቀው ነው »

የ74 ዓመቱ ጋውክ ጀርመን ለዓለም ዓቀፍ ውዝግቦች መፍትሄ በመሻት ረገድ ወደ ኃላ ከማፈግፈግ ይልቅ በበአፋጣኝ ድርሻዋን እንድትወጣ በቅርቡ ማሳሰባቸው በጀርመን ህብረተሰብ ዘንድ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ ዘልቋል ። በጀርመን ህገ መንግሥት ፕሬዝዳንቱ የክብር ምልክት እንጂ የፖለቲካ ወሳኝነት ሚና የለውም ። ጋውክ የፕሬዝዳንትነቱን ሥልጣን የተረከቡት መጋቢት 2004 ዓም ነው ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ