1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ብይን

ሐሙስ፣ የካቲት 25 2002

ካርልስሩኽ የሚገኘው የጀርመን ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፣ የጀርመን መንግስት የስልክ እና የኢሜል እንዲሁም የኢንተርኔት ግንኙነት መረጃዎች ለስድስት ወራት ተመዝግበው እንዲያዙ የሚያዘውን ህግ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ መሻሩ ለበርካታ የህጉ ተቃዋሚዎች እንደ ታላቅ ድል ተወስዷል ።

https://p.dw.com/p/MJrw
ምስል picture-alliance/ dpa
ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናትን ጨምሮ ፖለቲከኞችና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጀርመናውያን የተቃወሙት ይህ የግል ሚስጥር ጥበቃን መብት ይጥሳል የተባለው ህግ ከትናንት በስተያ በመሻሩ ብዙዎች ከመሰለል እፎይታ ያገኙ ያህል ተደስተዋል ። የህጉ ተቃዋሚዎች ያስገቡትን አቤቱታ የመረመረው ፍርድ ቤት ማክሰኞ ባሳለፈው ውሳኔ በህጉ መሰረት እንዲቀመጡ የተደረጉ የስልክ የኢሜልና የኢንተርኔት ግንኙነት መረጃዎች በሙሉ እንዲሰረዙ አዟል ። ይሁንና ብይኑን ጠልቀው የተመለከቱ እንደሚሉት ለፀጥታ ቁጥጥር ሲባል መሰል መረጃዎችን ማስቀመጥና መከታተል ፈፅሞ ይቀራል ማለት አይደለም ። የዛሬው ዝግጅታችን ዓብይ ትኩረት ነው ። ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ