1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ምርጥ ዩኒቨርስቲዎች

ረቡዕ፣ ሰኔ 6 2004

በትምህርትና በምርምር ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ላይ ለመገኘት፣ የዩንቨርስቲዎችን ሁለንተናዊ አቋም ይበልጥ ማደርጀት እንደሚበጅ ጀርመን አጥብቃ ታምናለች። ስለሆነም፣ በትምህርትና ምርምር ሙሉ ዝግጅት የሚያደርጉትንና

https://p.dw.com/p/15Dvz
Humboldt Universität feiert 200. Jubiläum. Quelle: hu200.de Copyright: Heike Zappe
የሁምቦልት ዩኒቨርሲቲምስል HU/Heike Zappe

ለወደፊቱም የተሻለ አቅድ የሚያወጡትን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፤ የትምህርትና ምርምር ሚንስቴር አወዳድሮ በመምረጥ፣ ጠቀም ያለ በጀት ይመድብላቸዋል። ከተመረጡት ዩንቨርስቲዎች መካከል፤ የጥቂቶቹን ይዞታ በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ዝግጅት እንዳስሳለን ።


በጀርመን ሀገር የተመረጡ 9 ዩንቨርስቲዎችን ደረጃ ለመጠበቅ፤ብሎም ለማሻሻል የሚደረገው የሥራ እንቅሥቃሴ ሁለተኛ ዙር መርኅ ግብር ባለፈው መጸው መጀመሩ የሚታወስ ነው። በተመደበው 2,6 ቢሊዮን ዩውሮ በጀት፤ እጅግ ከፍ ያለ ደረጃ የተሰጣቸው ዩኒቨርስቲዎች፣ ይህንኑ ደረጃቸውን እንደጠበቁ እንዲቀጥሉ ነው የሚጠበቅባቸው። በአሁኑ ጊዜ፣ ብሩኅ ተስፋ ያላቸውና በትምህርትና ምርምር ሚንስቴር የተመዘገቡት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ 7 ናቸው። እ ጎ አ በ 2007 ይህ ፕሮጀክት ሲጀመር ፣ 9 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወይም ዩኒቨርስቲዎች ነበሩ የልኂቃን ዩኒቨርስቲዎች እንዲሆኑ የታጩት ። እነርሱም ፤
1, የበርሊኑ ነጻ ዩኒቨርስቲ
2, የገኧቲንገኑ ጊዎርግ አውጉስት ዩኒቨርስቲ፣
3, የአኸኑ የቴክኒክ ከፍተኛ ተቋም፣
4, የሃይድልበርጉ Ruprecht Karl ዩኒቨርስቲ ፤
5, የካርላስሩኸ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ፣
6, የፍራይቡርጉ የአልበርት ሉድቪግ ዩኒቨርስቲ፣
7, የኮንስታንትዝ ዩኑቨርስቲ
8, የሙዑንሸኑ ሉድቪኽ ማክስሚላን ዩንቨርስቲ እንዲሁም
9, የሙዑንሸኑ የቴክኒክ ዩንቨርስቲ ነበሩ።
በአሁኑ ጊዜ፣ በላቀ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተመሠከረላቸው ቀደም ሲል እንዳወሳነው 7 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ናቸው።
እነርሱም፤ የ Bochum, Köln, Bremen, Mainz , Tübingen, የድረስደኑ
የሥነ ቴክኒክ ዩንቨርስቲና የበርሊኑ Humboldt ዩኚቨርስቲ ናቸው።
ለዛሬ ፣ ከ 7ቱ መካከል ስለ 4ቱ ጥቂት የምንለው ይኖረናል ፤ በመጀመሪያ በጥንታዊቷና ዘመናዊቷ የጀርመን መዲና የሚገኘው ሁምቦልት ዩንቨርስቲ---
በበርሊኑ የአልክሳንደር ፎን ሁምቦልት ዩንቨርስቲ ፣ እ ጎ አ ከ 2009 ዓ ም አንስቶ በዚያ ስለ ባህልና ማኅበራዊ-ነክ መልክዓ ምድር የሚያስተምሩት ፕሮፌሰር Ilse Helbrecht ፣ የሁምቦልት ዩኒቨርስቲ የወደፊት መጻዔ ዕድል ብሩኅ ሆኖ ነው የሚታያቸው። እርሳቸውና 6 ሌሎች ፕሮፌሰሮች፣
የዩንቨርስቲው ሠራተኞችና ተማሪዎች፣ የአያሌ ዘመናት ታሪክ ያላቸው የጀርመን ዩንቨርስቲዎች ፣ በተኃ,ድሶ ለውጥ የሚሻሻሉበትን ጽንሰ ሐሳብ በጽሑፍ አቅርበዋል። ወደፊት ለማየት፤ ኢልዘ ሄልብሬኽት፣ ያለፈውን ተመልሶ መመልከቱ ይበጃል ባይ ናቸው። ለምሳሌም ያህል እ ጎ አ በ 1810 ዩንቨርስቲውን የመሠረቱት ወገኖች ራእይ ምን እንደነበረ መለስ ብሎ ማሰብ ማሰላሰሉ ጠቀሜታ አለው ነው የሚሉት።
«ቪልሄልም ፎን ሁምቦልት፣ ለምርምር ተግባር፤ ለመምህራን ሥራና ለተማሪዎች የመማር ጥረት ዐቢይ ትርጉም እንዲሰጣቸው ያደረጉ ነበሩ።»
በአሁኑ ጊዜ በበርሊኑ የሁምቦልት ዩንቨርስቲ፤ 40,000 ያህል ሰዎች ናቸው ፤ በትምህርት፤ በማስተማርና በምርምር ተግባር ላይ ተሠማርተው የሚገኙ ። የሚሰጠው ትምህርት ፣ የሚካሄደው ምርምር ፤ በፍልስፍና ዘርፎች፣ በሥነ ልሣናት፤ በታሪክ፣ በማዕከላዊው በርሊን በሚገኙ በፕረሺያ(ፕሮይሰን) ያማሩ የህንጻ ሥራዎች ላይ ፣ በህክምናና በተፈጥሮ የሳይንስ ዘርፎች ነው። በከተማይቱ መዳረሻ በአድለርስሆፍ የሚገኘው አዲሱና እጅግ ዘመናዊው የሳይንስ ጣቢያ ደግሞ ፤ የተለየ ትርጉም የሚሰጠው ነው። የሁምቦልት ራእይ፤ ኢልዘ ሄልብሬኽት እንደሚሉት፤ ለሁሉም የሚሠራ ነው። በተለይ ለወደፊቱ!
«ከዩንቨርስቲው ቅጥ(ጽ)ር ግቢ ታዋቂ ምሁራንን ማፍራት ነው የምንፈልገው። ከተማሪዎችና ፤ ከአስተዳደሩ አንስቶ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን ድረስ !
ከሞላ ጎደል በግለሰቦች ጥረትና ተሰጥዖ ላይ ነው የምናተኩረው ፤ ምክንያቱም ይህ በቀጥታ የሁምቦልት ራእይም ሆነ ግብ ነውና!»
ከበርሊን ፤ ብሬመንን ፤ ቦሆምንና ኮሎኝን አልፈን ከኮሎኝ በስተደቡብ ምሥራቅ በራይንላንድ ፋልትዝ ፌደራል ክፍለ ሀገር ርእስ ከተማ በማይንትዝ ወደሚገኘው የዮሐንስ ጉተንበርግ ዩንቨርስቲ እናምራ! በጀርመን ከሚገኙት ዩንቨርስቲዎች ሁሉ ከዋናው ባቡር ጣቢያ ቀረብ ብሎ መሃል ከተማ ውስጥ የሚገኝ የማይንትዝ ዩንቨርስቲ ነው።ብዙዎቹ «ፋክልቲዎች» በዚያው በዋናው ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው የሚገኙት።
እ ጎ አ በ 1400 ዓ ም ገደማ በዚያችው ከተማ በተወለደው የማተሚያ መሣሪያ በሠራው በዚህ ታዋቂ ሰው ስም የሚጠራው ዩንቨርስቲ እ ጎ አ በ 1477 ነው የተመሠረተው። ማተሚያ መሣሪያን ፣ በመጀመሪያ የጥንት ቻይናውያን ይሥሩት እንጂ መጽሐፍትንና ጋዜጦችን ለማተም በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጊዜ ሠርቶ ሥራ ላይ ያዋለው ጀርመናዊው ዮሐንስ ጉተንበርግ ነው። እጅግ በጣም ጥሩ በሚያሰኝ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዩንቨርስቲ ለወደፊት ይበጃል ብሎ ያቀረበው ጽንሰ ሐሳብ ፣ ዓላማውና ግቡ ምን ይሆን!? የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት GEORG KRAUSCH
«በትክክል ትኩረት በሰጠናቸው ዘርፎች ላይ ከሞላ ጎደል አንድ ነገር መደረግ ስላለበት፤ ገንዘብ ሥራ ላይ ማዋል እንሻለን። ይህንንም የምናከናውነው፤ ምንጊዜም በተሟሉ መዋቅሮች፣ እንዲሁም፣ በግል ተመራማሪዎችና ታዋቂ መምህራን ድጋፍ ይሆናል።»
የማይንትዙ የዮሐንስ ጉተንበርግ ዩንቨርስቲ ድጎማ እስካልተጓደለበት ጊዜ ድረስ በዚያ ከፍተኛ ትምህርታቸውን የሚከታተሉት 36 ሺ ገደማ የሚሆኑት ተማሪዎች በከፍተኛው የምርምር ተግባር ተጠቃሚዎች መሆናቸው የማይቀር ነው። ዩንቨርስቲው፣ ወደፊት የሚከተለውን መርኅ አስመልክቶ ያቀረበው ጽንሰ -ሐሳብ ባይሠምር እንኳ፤ በ 1477 የተመሠረተው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም፣ ዝናውን እንደጠበቀ የሚዘልቅበት ሁኔታ ተሣክቷል ባይ ናቸው ፣ ፕሬዚዳንቱ ።
ቀደም ሲል ከተዘረዘሩት ማለፊያ ስም ካገኙት 7 ዩንቨርስቲዎች መካካል አንዱ በደቡባዊው ጀርመን የሚገኘው የ Tübingen ዩንቨርስቲ ነው። በ 2007 በተደረገው ፍተሻ ፣ ያሁኑን ዓይነት የመመረጥ ዕድል አልገጠመውም ነበር። ቱዑቢንግን፤ እንደገና በመላ ጀርመን ፣ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ በሚገኙና ፣ በሚያመለክቱ ዘንድ ማለፊያ ስም ነው ያለው። ስለዚህ ከሚመሠክሩት መካከል ለምሳሌ፣ በዚያ ፣ የመገናኛ ብዙኀን ትምህርት ተከታታዮች፣ ኤቭገኒና ዳንኤለ የተባሉት ተማሪዎች ይገኙበታል።
2,«ቱዑቢንገን፣ ትንሽ ሆኖም ትልቅ ስም ያለው ዩንቨርስቲ ሲሆን፤ ከጀርመን ውጭ ሳይቀር የታወቀ ነው። የቱዑቢንገን ዩንቨርስቲ የሚቀበለኝ መሆኑን እንዳረጋገጥሁ በጣም ነበረ ኩራት የተሰማኝ። ምክንያቱም ፣ ዩንቨርስቲው ታዋቂ ስምና የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው በመሆኑ ነው። የዝህን ያህል ዝና ሌሎቹ ዩንቨርስቲዎች የላቸውም። ቱዑቢንገን ፣ በጀርመን እጅግ በጣም ጥሩ ከሚባሉት ዩንቨርስቲዎች አንዱ ነው። በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች መንበሩን የያዙ ትልቅ ችሎታ ያላቸው ፕሮፌሰሮችም ይገኙበታል። ስለሆነም የቱዑቢንገን ዩንቨርስቲ፣ እጅግ በጣም ጥሩ ለሚያሰኝ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ መቅረቡ፣ ጠቃሚና ትክክለኛ እርምጃ ነው እላለሁ።»
የቱዑቢንገን ዩንቨርስቲ፣ የልኂቃን(«ኤሊት ዩኒ») ሆኖ እንዲቀጥል ሁኔታዎችን በሚገባ ካመቻቸ፤ በባችለርና ማስተርስ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች እምብዛም የሚያሳየው ለውጥ አይኖርም። የበለጠ ትኩረት የሚደረገው በከፍተኛ ምርምር ላይ ይሆናል። የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ይበልጥ ለማሻሻል ፤ የዩንቨርስቲው ዋና ኀላፊ Bernd Engler እንደሚሉት ሌሎች መርኀ ግብሮች ተነድፈዋል፤። በትክክል ፣ የምርጥ ተማሪዎች ዩንቨርስቲ ለመባል ቱዑቢንገን፤ ያልተስተካከሉ የአሠራር ዘዴዎች እጅጉን መለወጥ ይኖርባቸዋል። በዚያ የሚገኘው የ 25 ዓመቱ የቱዑቢንገን ዩንቨርስቲ ተማሪ ቶቢያስ እንደሚያስበው፤ ተማሪዎች፤ በላቀ ሁኔታ የአማካሪዎችን ምክርና ክብካቤ የሚያገኙበት ዕድል ሊሰጣቸው ይገባል።
5,«ዩንቨርስቲው የልኂቃን ዩንቨርስቲ የሚል ልዩ ደረጃ ለማግኘት ብቁ ነው? አይደለም ? ለማለት እቸገራለሁ። በዩንቨርስቲው፣ ከትምህርት ነኩ ተቋም ይልቅ የመገናኛ ብዙኀኑ ክፍል ይበልጥ የተደራጀ ነው። የትምህርት ክፍሉ አደረጃጀት ፍጹም እንዳልሠመረ ማየት ይቻላል። በዐውደ ጥናት ለመሳተፍ፤ ለመገኘት እጅግ ያስቸግራል፤ የፈተና ውጤትም አልተሰጠንም። ምስቅልቅሉ የወጣ አሠራር ነው የሚታየው። እንዲህ ዓይነት አሠራር የሚከሠትበት ዩንቨርስቲ ፤ የልኂቃን ከፍተኛ የትምህርት ተቋም፤ ሊባል የሚችል አይመስለኝም።»
በቀድሞዋ ምሥራቅ ጀርመን ከምሥራቅ በርሊኑ ሁምቦልት ዩንቨርስቲ ሌላ ታዋቂውና በአጠቃላይ ከ 10 የጀርመን ምርጥ ዩንቨርስቲዎች መካከል አንዱ በሳክሰን(ሳክሰኒ)ፌደራል ክፍለ ሀገር ርእሰ ከተማ ድሬስደን የሚገኘው የሥነ ቴክኒክ ዩንቨርስቲ ነው።
36,500 ተማሪዎች ይገኙበታል። ይኸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም፤በይፋ ስሙ የድሬስደን የሥነ ቴክኒክ ዩንቨርስቲ መባሉ የዩንቨርስቲው አስተዳዳሪ Hans-Müller Steinhagen ትንሽ የሚያሳስት ነው።
«የሥነ ቴክኒክ ዩንቨርስቲ ነው ተብሎ የሚጠራው ወይም በእንዲህ ነው የምንታወቀው፤ ነገር ግን በጀርመን ሀገር፣ የተሟላ ደረጃ ካላቸው ጥቂት ዩንቨርስቲዎች አንዱ ነው። ከተፈጥሮ ሳይንስ ፤ ከኢንጅኔሪንግ ፤ ከህክምና ሳይንስና ከመሳሰለው ሌላ 12,500 ተማሪዎች፤ በተለያዩ የማኅበራዊ፣ ፍልስፍናና ባህል ዘርፎች በመሠማራት ትምህርታቸውን ይከታተላሉ።»
አሁን በተጠቀሰውና በሌሎቹም ዩንቨርስቲዎች ከአዳጊ አገሮች የመጡ የከፍተኛ ትምህርት ተከታታዮች ተመርቀውባቸዋል። በአሁኑ ጊዜም በተጠቀሱት ዩንቨርስቲዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ፤ የአዳጊ አገሮች ተወላጆች ፣ ጥቂቶችም ቢሆኑ ፣ኢትዮጵያውያንም እንደሚገኙባቸው የታወቀ ነው።

Johannes Gutenberg-Universität Mainz, Forum, eingestellt am 22.12.2009, Foto: Hartmann Fotodesign
የማይንስ ዩኒቨርሲቲምስል Hartmann Fotodesign
Ein Passant geht am Dienstag (10.10.2006) am Eingang zur Neuen Aula der Eberhard-Karls-Universität in Tübingen vorbei. Beim jüngst veröffentlichten Hochschulranking der Deutschen Forschungsgemeinschaft (DFG) landete die Eberhard-Karls-Universität in Tübingen auf dem 8. Platz. Damit zählt die Universität mit ihren 23 000 Studenten zu Deutschlands Spitzenhochschulen - und hat so die besten Voraussetzungen, von 2007 an Gelder aus der so genannten Exzellenzinitiative zu erhalten. Foto: Bernd Weißbrod dpa/lsw (Zu lsw-Korr: "Für Tübingen könnte der nächste Freitag zum Glückstag werden" vom 10.10.2006) +++(c) dpa - Report+++
የቱቢንገን ዩኒቨርሲቲምስል picture-alliance/dpa
Bundesbildungsministerin Annette Schavan (CDU) gibt am Mittwoch (23.03.2011) in Berlin eine Pressekonferenz. Schavan informierte zum Thema "Anerkennung ausländischer Abschlüsse". Foto: Hannibal dpa/lbn
ሚንስትር አኔተ ሻቫንምስል picture alliance/dpa

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ